በ2016 ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ዩጋንዳዊ አጥቂ ከቡድኑ ጋር እንደሚቆይ ታውቋል።

ዩጋንዳዊው አጥቂ ሲሞን በ2015 መጀመሪያ ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የጣና ዋንጫ የሀገሩን ክለብ ቡል ወክሎ በመጫወት የውድድሩ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ መሆኑ ሲታወቅ በዛው ዓመት ለኢትዮጵያ መድን ፊርማውን አኑሮ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጋር ራሱን ካስተዋወቀ በኋላ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስኬታማ ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል።
አሁን ውሉ ማለቁን ተከትሎ ለተጨማሪ ዓመት በንግድ ባንክ ለመቆየት መስማማቱን አውቀናል። ሲሞን ፒተር በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በ34 ጨዋታ በ2845 ደቂቃዎች ላይ ተሳትፎ በማድረግ ስምንት ጎሎችን በማስቆጠር የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆኑን ይታወቃል።

