ፉዐድ ፈረጃ ከፈረሰኞቹ ጋር ልምምድ ጀምሯል

ፉዐድ ፈረጃ ከፈረሰኞቹ ጋር ልምምድ ጀምሯል

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች እራሱን ለማጠናከር እየሰራ ይገኛል

ከፋይናንስ ችግር ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የቆየው አንጋፋው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፋይናስ ችግሩ ተቀርፎ በተሻለ ቁመና ለመገኘት እየሰራ ይገኛል።

ቡድኑ በሚቀሩት ስምንት ጨዋታዎች ላይ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ከወራጅ ስጋቱ ለመላቀቅ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ለመቀላቀል እየሰራ እንደሆነም አውቀናል። በዚህም መነሻነት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው እና ያለፈው አንድ ዓመት በጉዳት ከሜዳ ርቆ የቆየው አማካዩ ፉአድ ፈረጃ ለማስፈረም በማሰብ ያለፉትን ሦስት ቀናት ከቡድኑ ጋር ልምምድ እየሰራ ይገኛል። በቀጣይ ቀናቶች ፉዐድ ለፈረሰኞቹ ይፈርማል ወይም አይፈርም የሚለው የሚወሰን ይሆናል።

 

በሌላ ዜና በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት የተመለሱት የቀድሞ የፈረሰኞቹ አለቃ ሰርዲዮቪች ሚሎቲን ( ሚቾ ) በሀገር ቤት በሚኖራቸው ቆይታ የቀድሞ ምክትላቸውን አሁን የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን እንደሚያማክሩ መገለፁ የሚታወቅ ሲሆን የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል አሰልጣኝ ሚቾ የምልመላውን ስራ እየሰሩ መሆናቸውንም አውቀናል።