ሐይቆቹ በነብሮቹ ቤት ቆይታ የነበረውን ተጨዋች አስፈረሙ

በሀድያ ሆሳዕና የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ወጣቱ ተከላካይ ቃለአብ ውብሸት ወደ ሀይቆቹ ለማምራት ተስማምቷል። ከታዳጊ ቡድን እስከ ዋናው ቡድን ለስድስት ዓመታት ለነብሮቹ ሲጫወት የቆየው ተከላካዩ አሁን ደግመ መዳረሻውን በእግርኳስ ህይወቱ ሁለተኛ ክለቡ ወደ የሚሆነው ሀዋሳ ከተማ አምርቷል። ቃለአብ በሀይቆቹ ቤት ለሁለት ዓመት ለመጫወት መስማቱም ታውቋል።
ዛሬ ወደ ዝውውሩ በመግባት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ዝውውሮችን እንደሚፈፅሙ ሰምተናል።

