ቢጫዎቹ ጋናዊው ተጫዋች በውሰት ለማስፈረም ተስማሙ

ቢጫዎቹ ጋናዊው ተጫዋች በውሰት ለማስፈረም ተስማሙ

የ70ኛ ዓመት የምስረታ በዓላቸውን በማክበር ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች ጋናዊው የፊት መስመር ተጫዋች ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሰዋል

ቀደም ብለው እዮብ አለማየሁ ፣ በረከት ሳሙኤል ፣ ካርሎስ ዳምጠው እና ማማዱ ሴክ ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አሁን ደግሞ ባለፉት ወራት ከአዞዎቹ ጋር ጥሩ ቆይታ የነበረውን ጋናዊው አብዱልራህማን መሐመድን ከመዳማ በውሰት ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

በውድድር ዓመቱ አጋማሽ ለተሻለ የጨዋታ ዕድል በውሰት ውል ከጋናው መዳማ ወደ አርባምንጭ ከተማ አምርቶ አራት ግቦችን በማስቆጠር ከአዞዎቹ ጋር ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው የፊት መስመር ተጫዋቹ በክለቡ ጥሩ ቆይታ ካደረገ በኋላ ዳግም በአንድ ዓመት የውሰት ውል ወደ ወልዋሎ አምርቷል። ከዚህ ቀደም የኤም ቲ ኤን ኤፍ ኤ ዋንጫ አሸናፊ በሆነበት ንሶትሬማን ጨምሮ በታንዛንያው Tanzanian Revenue Authority (TRA) ፣ መዳማ እና በአርባምንጭ ከተማ መጫወት የቻለው አብዱልራህማን አሁን ደግሞ በአንድ ዓመት የውሰት ውል ወደ ወልዋሎ አምርቷል።