በካፍ ኮንፌደሬሽን ዋንጫ ለሚጠብቀው የማጣሪያ ጨዋታ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ወልዋሎ
አምስት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን አሳደገ

ከሱዳኑ ሂላል አል ሳሕል ጋር ላለባቸው የካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ጨዋታ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኙት ወልዋሎዎች ራሳቸውን ለማጠናከር የነባሮችን ውል በማደስ እና አዳዲስ ተጫዋቾች በማስፈረም በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አምስት ተጫዋቾች ወደ ዋናው ቡድን ማሳደጋቸው ታውቋል። አማኑኤል ተወልደ ፣ ሄርሞን ሃይላይ ፣ ሚኪኤለ ገብረ፣ ዮናስ መዝገቦ እና ዓማር መሐመድ ደግሞ በአሰልጣኝ ተስፋአለም አክሊሉ እየተመራ በክልላዊ ውድድሮች ጥሩ እንቅስቃሴ ካደረግው ሁለተኛ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን ያደጉ ተጫዋቾች ናቸው።

