” ..እኔ እንዳውም ምሳሌ የሚሆን የምርጫ ሂደት ይሆናል ብዬ ነው የምጠብቀው ”

አቶ ኢሳያስ ጅራ ጋዜጣዊ መግለጫቸውን ሰጥተው አጠናቀዋል። በመጨረሻም ምርጫው ሁሉን ያማካለ ፍትሐዊ ነው ብለው ያስባሉ ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል።
የምርጫ ሂደቱ ተጭበርብሯል የሚለው አልገባኝም። ጠቅላላ ጉባኤው ባስቀመጠው ህግ እየሄደ ነው፤ በምን ምክንያት ፍትሐዊ አይደለም እንደተባለ አልገባኝም። እኔ እንዳውም ምሳሌ የሚሆን የምርጫ ሂደት ይሆናል ብዬ ነው የምጠብቀው። እኔ እንደ ማንኛውም ተወዳዳሪ እራሴን እጩ አድርጌ ማስገባቴን ነው የማቀው ከዚህ ውጭ ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም ተጨርብሯል የሚባለው ትክክል አይደለም ብለዋል።

