የጋናዊው ግብ ጠባቂ ማረፊያው ታውቋል

የጋናዊው ግብ ጠባቂ ማረፊያው ታውቋል

በሽረ ምድረ ገነት ቆይታ የነበረው ጋናዊ የግብ ዘብ ወደ ሌላ የሀገራችን ክለብ አምርቷል።

በተጠናቀቀው የውድደር ዓመት ወደ ሀገራችን መጥቶ ዓመቱን ከሽረ ምድረ ገነት ጋር ያሳለፈው ጋናዊው ግብ ጠባቂ ሪችሞንድ አዬ ወደ ሌላው የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ለመፈረም ከስምምነት ደርሷል። ጋናዊው ለማስፈረም የተስማማው ክለብ ደግሞ ኢትዮጵያ መድን ነው። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በ35 ጨዋታዎች ተሳትፎ 3077 ደቂቃዎችን ቡድኑን ያገለገለው ይህ ግብ ጠባቂ ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት በሀገሩ ክለቦች ዋፋ ፣ ኸርትስ ኦፍ ኦክ እና ዲሪምስ ቆይታ ማድረጉም ይታወሳል።