ኢትዮጵያውያን ዳኞች የታዳጊዎችን ውድድር እየመሩ ነው

ኢትዮጵያውያን ዳኞች የታዳጊዎችን ውድድር እየመሩ ነው

ሁለት ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ታንዛኒያ ይገኛሉ።

በታንዛኒያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ላይ ሁለቱ ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ውድድሩን ከሚመሩ ዳኞች መካከል መሆናቸውን አረጋግጠናል።

ዋና ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ እና ረዳት ዳኛ ሙስጠፋ መኪ የውድድሩን የመክፈቻ ጨዋታ የመሩ ሲሆን በቀጣይ የሚደረጉ ሌሎች ጨዋታዎችንም እንደሚመሩ ሶከር ኢትዮጵያ አውቃለች።

እዚህ ውድድር ላይ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ 7 ሰዓት ላይ ከሩዋንዳ ጋር የሚያደርግ ይሆናል።