በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚጫወቱ ስድስት ተጫዋቾች ሀገራቸውን በመወከል በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል

በ2027 በኬኒያ ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጣምራ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች በሕዳር ወር ይካሄዳሉ። ቀደም ብሎ ራሱን ከዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ያገለለው የሲዳማ ቡናው ካሊድ አውቾ በደጋፊዎች በክብር እንዲሸኝ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ እንደቀረበለት የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአማካዩ በተጨማሪ በሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተጫወቱ የሚገኙ ስድስት የውጪ ሀገር ተጫዋቾች ሀገራቸውን በመወከል በውድድሩ እንዲሳተፉ ጥሪ እንደቀረበላቸው ታውቋል።
– የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አጥቂ ካሌብ ስቲፍ ለዋናው እና ከ23 ዓመት በታች የጋቦን ብሔራዊ ቡድን
– የሀዋሳ ከተማው ግብ ጠባቂ ሴርጌ ኦባሳ እና
የፋሲል በከነማው አማካይ ሮማሪክ ዲንሆ
ለቤኒን ብሔራዊ ቡድን
– የመቻሉ ግብ ጠባቂ መሐመድ ካማራ ለጊኒ ብሔራዊ ቡድን
– የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ የተከላካይ አማካዩ ሰይዱ ባህ ካማራ እና የወላይታ ድቻው አማካይ ሳይዱ ፎፋና ለሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ላይ ሀገራቸውን የሚያገለግሉ ይሆናል።

