ዛሬ በጀመረው የዋልያዎቹ ዝግጅት አንድ ተጫዋች በጉዳት ምክንያት ቡድኑን ሳይቀላቀል ሲቀር በምትኩ አዲስ ተጫዋች ቡድኑን ተቀላቅሏል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርጋቸው 3ኛ እና 4ና ምድብ ጨዋታዎች ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት የጀመረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት አቤል ያለውን በጉዳት ምክንያት በቢኒያም ፍቅሩ የተካው የዋልያዎቹ ስብስብ ዛሬም ጉዳት በገጠመው የኢትዮጵያ ቡና የመስመር ተከላካይ አብዱልሰላም የሱፍ ምትክ ለሲዳማ ቡናው የመስመር ተከላካይ ኤፍሬም ታምራት ጥሪ አድርጎ ተጫዋቹ ልምምዱን አብሮ ጀምሯል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በነበረው የመጀመርያ የልምምድ መርሐግብር ኩዌት ከሚገኙት ከነዓን ማርክነህ እና ጋቶች ፓኖም በቀር 21 ተጫዋቾች በዛሬው ልምምድ ላይ ተገኝተዋል።

