የኢትዮጵያ እና የጋና ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኖች የዛሬ የልምምድ ውሎ

ዛምቢያ ለምታስተናግደው የ2017 የአፍሪካ ከ20 አመት በታች ዋንጫ 1ኛ ዙር ማጣርያ ኢትዮጵያ ከ ጋና በመጪው እሁድ ይጫወታሉ፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ቡድን በአዲስ አበባ ስታድየም ልምምዱን ሲቀጥል ትላንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት ጋናዎች ደግሞ በባንክ ሜዳ ልምምዳቸውን አከናውነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን በዛሬው የልምምድ ውሎው የአዲስ አበባ ስታድየም መሀል ሜደውና ጎሉ አካባቢ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨቀይቱና የተወሰኑ ጥገና በመደረጉ ምክንያት እንደሚፈለገው ልምምድ ለመስራት የተቸገሩ ሲሆን ደረቅ ባለው የሜዳው ክፍል ለመስራት ችለዋል ።

በእሁዱ ጨዋታ የመጀመርያ ተሰላፊ ይሆናሉ። ተብለው የሚጠበቁ ተጨዋቾችን በመለየት በመከላከልና በማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገ ልምምድ የዛሬው ልምምድ አካል ነበር፡፡ በትጥቅ ረገድ የነበሩትን ክፍተቶችን በቀረፈ መልኩም ሁሉም በአንድ አይነት ማልያ ልምምዳቸውን ሰርተዋል፡፡

የጅማ አባ ቡናው ኪዳኔ አሰፋ እና የሙገሩ ተመስገን አዳሙ በፓስፖርት ጉዳይ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ያልሰሩ ሲሆን በአቋም መፈተሻ ጨዋታ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረው አሜ መሃመድ ከጉዳቱ አገግሞ ልምምዱን ሰርቷል፡፡

PicsArt_1463773708414

ትላናት አመሻሹ ላይ አዲስ አበባ በመግባት አፋራሲስ ሆቴል ማረፍያውን ያደረገው የጋና ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዛሬ  ልምምዱን በሲኤምሲ አካባቢ አዲስ በተገነባው የኢትዮዽያ ንግድ ባንክ ሜዳ 10:00 ላይ ልምምዱን አከናውኗል፡፡

ሁለት ሰአት በፈጀ ልምምዳቸው በዲፓርትመንት በተከፋፈለ ሁኔታ የተለያዩ ልምምዶችን ሲሰሩ የመስመር ላይ ኳሶችና ተሻጋሪ ኳሶችን እንዴት ወደ ውጤት መቀየር እንዳለባቸው በተለየ ሁኔታ ጠንካራ ልምምድ ሲሰሩ ለማየት ችለናል፡፡

የጋና ከ20 አመት በታች ቡድን ነገ በ10:00 እሁድ በሚጫወቱበት አዲስ አበባ ስቴዲዮም የመጨረሻ ልምምዳቸውን የሚሰሩ ይሆናል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *