ኢትዮጵያ ቡና 2-1 ሀዲያ ሆሳእና
59′ አብዱልከሪም መሀመድ
89′ ፓትሪክ ቤናውን
19′ እንዳለ ደባልቄ
– – – – –
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የማሸነፍያውን ግብ ያስቆጠረው ፓትሪክ ከደጋፊው ጋር ደስታውን በመግለፅ ላይ ይገኛል፡፡
90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡
89′ ጎልልል!!! ቡና
ፓትሪክ ቤናውን ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ቡናን መሪ አድርጓል፡፡
88′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
እያሱ ታምሩ ወጥቶ አማኑኤል ዮሃንስ ገብቷል፡፡
86′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
ዱላ ሙላቱ አምራላ ደልቻታን ቀይሮ ገብቷል፡፡
82′ ቡና የአቻነቱን ግብ ካስቆጠረ በኋላ ጨዋታው የተቀዛቀዘ ሲሆን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ይህ ነው የሚባል የግብ ማግባት ሙከራ አልታየም፡፡
የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
አበው ታምሩ ወጥቶ ኢማኑኤል አኪራሺ ገብቷል፡፡
*በአሁኑ ሰአት ቡና በፊት መስመር 3 ካሜሩናዊያንን እያጫወተ ይገኛል፡፡ ይህ ጨዋታ ለንዳዬ ፋይስ የመጀመርያ የቡና ጨዋታ ነው፡፡
63′ የተጫዋች ለውጥ – ኢትዮጵያ ቡና
ፓትሪክ ቤናውን እና ንዳዬ ፋይስ ገብተው ኤልያስ ማሞ እና ጥላሁን ወልዴ ወጥተዋል፡፡
59′ ጎልልል!!!
አብዱልከሪም በፍፁም ቅጣትምት ክልል ውስጥ ወደ ግብ የመታው ኳስ ከመረብ አርፏል፡፡
55′ ጥላሁን ከግራ መስመር ወደ ግበ ብየሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
48′ አምራላ ከተከላካዮች መሃል አምልጦ ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ቢገኝም ወንድይፍራው እና ኤፍሬም ደርሰው አስጥለውታል፡፡ የሆሳእና ተጫዋቾች ፍፁም ቅጣት ምት ይገባናል ብለው ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡
46′ ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
– – – –
*የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች አመራሮቹ ከሃላፊነት እንዲነሱ በተቃውሞ መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡
ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በሀዲያ ሆሳእና መሪነት የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቀቀ፡፡
40′ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ልክ 40ኛው ደቂቃ ላይ በቡና አመራሮች ላይ በጩኸት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡
37′ ኤልያስ ማሞ ከጥላሁን ጋር አንድ ሁለት ተቀባብሎ ወደ ሆሳእና የግብ ይዞት የገባውን ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ሰዶታል፡፡
*ቡና ግብ ለማስቆጠር ወደ ሆሳእና የግብ ክልል ቢጠጉም ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡ ሆሳእናዎች በአንፃሩ በመከላከልና በፈጣን መልሶ ማጥቃት የግብ እድል ለመፍጠር በመጣር ላይ ይገኛሉ፡፡
33′ መስኡድ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ጃክሰን አውጥቶበታል፡፡
29′ ጥላሁን ወልዴ ከቀኝ የፍፁም ቅጣት ምት ጠርዝ የሞከረው ኳስ ወደውጪ ወጥቶበታል፡፡
19′ ጎልልል!!!
እንዳለ ደባልቄ ከግራ መስመር ወደ ውስጥ አጥብቦ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ በሀሪሰን መረብ ላይ አርፏል፡፡ ግሩም ጎል፡፡
16′ ጥላሁን ወልዴ ለአብዱልከሪም ጥሩ ኳስ ቢያሻግርለትም ጃክሰን ቀድሞ በመውጣት ይዞታል፡፡
11′ እንዳለ ደባልቄ ከመስመር ያሻገረውን ኳስ አምራላ በግንባሩ ገጭቶ ቢሞክርም ሀሪሰን በአስገራሚ ቅልጥፍና አውጥቶበታል፡፡
9′ ኤልያስ ማሞ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ አግዳሚውን ለትሞ ተመልሷል፡፡
8′ አምራላ ደልታታ በረጅሙ የተላከለትን ኳስ ተቆጣጥሮ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
1′ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ ሀዲያ ሆሳዕና ከግራ ወደቀኝ ቡና በተቃራኒው አቅጣጫ ያጠቃሉ፡፡
የኢትዮጵያ ቡና አሰላለፍ
ሀሪሰን ሀሶው
አብዱልከሪም መሀመድ – ወንድይፍራው ጌታሁን – ኤፍሬም ወንድወሰን- ሳለአምላክ ተገኝ
ጋቶች ፓኖም – መስኡድ መሃመድ
እያሱ ታምሩ – ኤልያስ ማሞ – ጥላሁን ወልዴ
ያቤውን ዊልያም
——-//——–
የሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ
ጃክሰን ፊጣ
ታረቀኝ ጥበቡ – እርቅይሁን ተስፋዬ – ቢንያም ገመቹ – ሄኖክ አርፊጮ
አምራላ ደልቻታ – አድናን ቃሲም – አበው ታምሩ – አበባየሁ ዮሃንስ – አየለ ተስፋዬ
እንዳለ ከበደ