ከፍተኛ ሊግ ፡ ጅማ አባ ቡና የምድቡን መሪነት ሲቆናጠጥ አማራ ውሃ ስራ ከሜዳው ውጪ ድል አስመዝግቧል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ትላንት መካሄድ የነበረባቸው ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገው ጅማ አባ ቡና እና አማራ ውሃ ስራ ከሜዳቸው ውጪ አሸንፈዋል፡፡ 

ወደ ባቱ ያቀናው ጅማ አባ ቡና ባቱ ከተማን 3-1 አሸንፎ የምድብ ለ መሪነትን ከአዲስ አበባ ከተማ ተረክቧል፡፡ የጅማ አባ ቡናን ሶስቱንም የድል ግቦች በማስቆጠር ሀት-ትሪከ የሰራው በተከታታይ ጨዋታዎች ለጅማ ውጤታማነት ቁልፍ ሚና እየተወጣ የሚገኘው ኪዳኔ አሰፋ ነው፡፡ የባቱን ብቸኛ ግብ አዳነ አሰፋ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ጅማ በድሉ ታግዞ የምድቡን መሪነት ከአዲስ አበባ ከተማ በ1 ነጥብ በመብለጥ ሲረከብ ባቱ ከተማ ባለበት 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የምድብ ለ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል

111itled

 

በምድብ ሀ አፄ ዘርአያእቆብ ስታድየም ላይ አማራ ውሃ ስራን ያስተናገደው ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን 3-2 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ አወዛጋቢ ክስተቶች በተስተናገዱበት ጨዋታ የአማራ ውሃ ስራን ግቦች ሀብታሙ ሽዋለም ሁለት ፣ ቃለፍቅር መስፍን አንድ አስቆጥረዋል፡፡ የባለሜዳውን ቡድን ግቦች ምህረት ለማ እና የአማራ ውሃ ስራ ተከላካይ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል፡፡ አማራ ውሃ ስራ በድሉ ታግዞ ደረጃውን ወደ 7ኛ ከፍ ሲያደርግ ሰሜን ሸዋ ባለበት የመጨረሻ ደረጃ ረግቷል፡፡

የምድብ ሀ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል

2222

 

የ8ኛ ሳምንት ውጤቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

ምድብ ሀ

ባህርዳር ከተማ 2-0 ወልድያ

መቐለ ከተማ 2-3 አክሱም ከተማ

ወሎ ኮምቦልቻ 1-0 ወልዋሎ

ሙገር ሲሚንቶ 0-0 ቡራዩ ከተማ

ሱሉልታ ከተማ 0-0 ሰበታ ከተማ

ፋሲል ከተማ 2-1 አአ ፖሊስ

ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት 0-2 ኢትዮጵያ መድን

ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን 2-3 አማራ ውሃ ስራ

 

ምድብ ለ

አዲስ አበባ ከተማ 0-0 አአ ዩኒቨርሲቲ

ሻሸመኔ ከተማ 0-0 ድሬዳዋ ፖሊስ

ጅማ ከተማ 1-3 ወራቤ ከተማ

ደቡብ ፖሊስ 4-4 አርሲ ነገሌ

ጅንካ ከተማ 0-0 ሀላባ ከተማ

ናሽናል ሴሜንት 4-0 ፌዴራል ፖሊስ

ባቱ ከተማ 1-3 ጅማ አባ ቡና

(ነቀምት ከተማ ከ ነገሌ ቦረና ለሌላ ጊዜ ተላልፏል)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *