ፕሪሚየር ሊግ ፡ ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ ፈራሚው የመጨረሻ ደቂቃ ጎል ታግዞ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ዛሬም ቀጥሎ ሲውል ኢትዮጵያ ቡና በመጨረሻ ሰአት ባገኘው ግብ ታግዞ ሀዲያ ሆሳዕናን 2-1 አሸንፏል፡፡

እንግዶቹ ሀዲያ ሆሳዕናዎች በቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ተስፋ ቡድን ተጫዋች እንዳለ ደባልቄ የ19ኛ ደቂቃ ጎል 1-0 መምራት ሲችሉ እስከ 58ኛው ደቂቃ ድረስም መሪነታቸውን ማስጠበቅ ችለው ነበር፡፡

ጨዋታው 40ኛ ደቂቃ ላይ ሲደርስ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የክለቡ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በተቃውሞ ጩኸት ገልፀዋል፡፡ የእረፍት ሰአቱንም በስታድየሙ የተገኙ የቡና አመራሮች ላይ ተቃውሞ በማሰማት አሳልፈዋል፡፡

በ58ኛው ደቂቃ የቀኝ መስመር ተከላካዩ አብዱልከሪም መሃመድ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ሲያደርግ ተቀይሮ የገባው ፓትሪክ ቤናውን በ90ኛው ደቂቃ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ለኢትዮጵያ ቡና ወሳኝ ሶስት ነጥቦች አስገኝቷል፡፡ በጥር ወር ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀለው ካሜሩናዊው ፓትሪክ በ2ኛ የነጥብ ጨዋታው የመጀመርያ ግቡን አስቆጥሯል፡፡

ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች በከፍተኛ ሀዘን ሜዳውን ሲለቁ ግብ አስቆጣሪው ፓትሪክ የቡና ደጋፊዎችን ሲያስጨፍር ተስተውሏል፡፡

ውጤቱ ኢትዮጵያ ቡናን 5 ደረጃዎች አሻሽሎ 7ኛ ደረጃ ላይ እዲቀመጥ ሲያደርገው ሀዲያ ሆሳዕና ከቀዳሚዎቹ በነጥብ ርቆ የሊጉ ግርጌን እንደያዘ እንዲቀጥል አድርጎታል፡፡

 

የደረጃ ሰንጠረዥ

st

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *