ኮንፌድሬሽን ካፕ፡ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ክለቦች ታውቀዋል 

 

የካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ ቅድመ ማጣሪያ ዙር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ተድርገዋል፡፡ እንደ ቻምፒየንስ ሊጉ ሁሉ የሰሜን አፍሪካ ቡድኖች ማጣሪያውን ለማለፍ የተቸገሩ አይመስልም፡፡ በአንፃሩ የምስራቅ አፍሪካ ክለቦች እንደከዚህ ቀደሙ በጊዜ ከውድድሩ መሰናበታቸውን ተያይዘውታል፡፡

ኢትዮጵያን የወከለው መከላከያ በግብጹ ምስር አል ማቃሳ በድምር ውጤት የ6-1 ሽንፈት ደርሶበት ከውድድሩ ውጪ ሆኗል፡፡

የሞሮኮው ካውካብ ማራካሽ የቡርኪናፋሶውን ዩኤስኤፌን በመለያ ምት 5-4 አሸንፏል፡፡ ካውካብ ማራካሽ ከሜዳው ውጪ 3-0 በመሸነፉ ነበር ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ያመሩት፡፡

የዩጋንዳው ስፖርት ክለብ ቪላ የሱዳኑን አል ካርቱም አል ዋታኒን 2-0 በማሸነፍ ወደ አንደኛው ዙር ሲያልፍ የኬኒያው ባንዳሪ በዲ.ሪ. ኮንጎ ሴንት ኢሎዪ ሉፖፖ 3-1 ተሸንፎ ከውድድር በጊዜ ተሰናብቷል፡፡

ቪክቶሪያ ክለብ ሞካንዳ፣ ሳግራዳ ኤስፔራንሳ፣ ቢድቬስት ዊትስ፣ ሬኔሳንስ፣ ሃራሬ ሲቲ፣ ስታደ ጋብሲየን፣ ናሳራዋ ዩናይትድ፣ ዲፖርቲቮ ሞንጎማ፣ አትሌቲኮ ኦሎምፒክ፣ ፖሊስ ወደ ቀጣዩ ዙር ካለፉት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በውድድሩ ላይ ከዚህ በኃላ ኢትዮጵያ በሁለት ተጫዋቾች የምትወከል ሲሆን የኡመድ ኡኩሪ ክለብ የሆነው ኢኤንፒፒአይ እና የአዲስ ህንፃ ክለብ አሃሊ ሸንዲ ከአንደኛው ዙር ጀምሮ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

የኒጀሩ ኤኤስ ሶኒዲፕ ከሊቢያው አል ኢቲሃድ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በኒያሚ ዓየር ማረፊያ በደረሰ ጥቃት ምክንያት ሌላ ግዜ ተላልፋል፡፡

የአንደኛው ዙር ጨዋታዎች

ዲፖርቲቮ ሞንጎማ (ኤኳቶሪያል ጊኒ) ከ ፋት ዩኒየን ስፖርት (ሞሮኮ)

ምስር አል ማቃሳ (ግብፅ) ከ ሲኤስ ዶን ቦስኮ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)

ካውካብ ማራካሽ (ሞሮኮ) ከ ባራክ ያንግ ኮንትሮለር (ላይቤሪያ)

ሬኔሳንስ (ቻድ) ከ ኤስፔራንስ (ቱኒዚያ)

አፍሪካ ስፖርትስ (ኮትዲቯር) ከ ኢኤንፒፒአይ (ግብፅ)

ሳግራዳ ኤስፔራንሳ (አንጎላ) ከ ሊጋ ዲስፖርቲቫ ዲ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)

ናሳራዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) ከ ሲኤስ ኮንስታንታይን (አልጄሪያ)

ቢድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) ከ አዛም (ታንዛኒያ)

ስታደ ጋብሲየን (ቱኒዚያ) ከ ኤስ ካሎም (ጊኒ)

ሃራሬ ሲቲ (ዚምባቡዌ) ከ ዛናኮ (ዛምቢያ)

ስፖርት ክለብ ቪላ (ዩጋንዳ) ከ ጄኬዩ ኤስሲ (ዛንዚባር)

ኤምሲ ኦራን (አልጄሪያ) ከ ስፖርቲንግ ክለብ ዲ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)

ኤኤስ ሶኒዲፕ (ኒጀር) / አል ኢቲሃድ (ሊቢያ) ከ ሜድኢአማ (ጋና)

ሴንት ኢሎዪ ሉፖፖ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) ከ አል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን)

አትሌቲኮ ኦሎምፒክ (ቡሩንዲ) ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)

ቪክቶሪያ ክለብ ሞካንዳ (ኮንጎ ብራዛቪል) ከ ፖሊስ (ሩዋንዳ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *