ኤሌክትሪክ 1-1 ወላይታ ድቻ
90+1′ ፒተር ኑዋድኬ
56′ በድሉ መርዕድ
ተጠናቀቀ
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
90+1′ ጎልልል!!!! ፒተር ኑዋድኬ በጠንካራ ምት ግብ አስቆጥሮ ኤሌክትሪክን አቻ አድርጓል፡፡
86’የተጫዋች ለውጥ ወላይታ ድቻ
አላዛር ፋሲካ ወጥቶ ስንታየሁ መንግስቱ ገብቷል፡፡
85′ ኤሌክትሪክ የአቻነት ግብ ለማግኘት ጫና ሲፈጥር ድቻዎች በተለይ በበድሉ መርዕድ አማካኝነት በመልሶ ማጥቃት ተጨማሪ ግብ ለማግኘት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
83′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
ተክሉ ታፈሰ ፀጋ አለማየሁን ቀይሮ ገብቷል፡፡
68’ቢጫ ካርድ
አሳልፈው ዘመድኩን በድሉ ላይ በሰራው ጥፋት የመጀመርያውን የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡
67′ የተጫዋች ለውጥ – ወላይታ ድቻ
ወንድማገኝ በለጠ ወጥቶ ሰለሞን ሀብቴ ገብቷል፡፡
64′ የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
ዋለልኝ ገብሬ ማናዬ ፋንቱን ቀይሮ ገብቷል፡፡
63‘ አሳልፈው ዘመድኩን ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ ፒተር በግንባሩ ገጭቶ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡
61′ የተጫዋች ለውጥ – ኤሌክትሪክ
ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ አሳልፈው መኮንን ገብቷል፡፡
56’ጎልልል!!!
በድሉ መርእድ የመታው ቅጣት ምት አሰግድ አክሊሉ በቀላሉ ለመያዝ ሲሞክር አምልጦት ወደ ግብነት ተቀይሯል፡፡
48′ አናጋው ባደግ ከመስመር ያሻገረው ኳስ አላዛር ጋር ሳይደርስ አልሳዲቅ እንደምንም አውጥቶታል፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ
– – – – –
ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ካለግብ ተጠናቋል፡፡
45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨምሯል
30′ የሁለቱም ቡድኖች ቅብብሎች ቶሎ ቶሎ እየተቋረጠ እና ወጥ ያልሆነ እንቅስቃሴ እየተመለከትን እንገኛለን
20′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡ ሁለቱም ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ቢቀርቡም የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡
*በክረምቱ ድቻን ለቀው ኤሌክትሪክን የተቀላቀሉት አሸናፊ ሽብሩ እና ተስፋዬ መላኩ ለመጀመርያ ጊዜ የቀድሞ ክለባቸውን እየገጠሙ ይገኛሉ፡፡
2′ አናጋው ባደግ ከቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ የግቡን ቋሚ መልሶታል፡፡
1′ ጨዋታው ተጀመረ
ድቻ ከቀኝ ወደ ግራ ሲያጠቃ ኤሌክትሪክ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃል፡፡
11:23 ሁለቱም ቡድኖች ሰውነታቸውን አፍታተው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡
የኤሌክትሪክ አሰላለፍ
አሰግድ አክሊሉ
አወት ገ/ሚካኤል – ተስፋዬ መላኩ – ሲሴይ ሀሰን – አልሳዲቅ አልማሂ
በሃይሉ ተሻገር – ደረጄ ሃይሉ – አሸናፊ ሽብሩ
ማናዬ ፋንቱ – ፍፁም ገብረማርያም – ፒተር ኑዋድኬ
የወላይታ ድቻ አሰላለፍ
ወንድወሰን አሸናፊ
አናጋው ባደግ – ሙባረክ ሽኩሪ – ቶማስ ስምረቱ – ፈቱዲን ጀማል
አማኑኤል ተሾመ – ዮሴፍ ድንገቱ- በድሉ መርዕድ – ወንድማገኝ በለጠ – ፀገ ጋአለማየሁ
አላዛር ፋሲካ
እንደምን ውላችኋል ክቡራት እና ክቡራን!!
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 12ኛ ሳምንት አአ ስታድየም ላይ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ድቻ የሚያደርጉት ጨዋታ 11:30 ላይ ይጀምራል፡፡ ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት በዚሁ ገፅ ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡
አብራችሁን ቆዩ!