ፕሪሚየር ሊግ ፡ ሀዋሳ ከተማ በተጨማሪ ደቂቃ ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን ሲያሸንፍ ሲዳማ ቡና ከዳሽን አቻ ተለያይተዋል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ 2 ጨዋታዎች ተካሂደው ሀዋሳ ከተማ ድል ሲቀናው ዳሽን ቢራ ከይርጋለም ነጥብ ይዞ ተመልሷል፡፡

ሀዋሳ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናገደው ሀዋሳ ከተማ 2-1 በጭማሪ ሰአት በተቆጠረ ግብ ታግዞ አሸንፏል፡፡ በዲሲፕሊን ጉዳይ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ በመታገዳቸው ምክንያት ጋዲሳ መብራቴ እና ታፈሰ ሰለሞንን ያላሰለፈው ሀዋሳ ከተማ በፍርዳወቅ ሲሳይ የ54ኛ ደቂቃ ግብ ቅድሚያውን የያዘ ሲሆን ቅዱስ ጊዮርጊስ በደጉ ደበበ የ78ኛ ደቂቃ ግብ አማካኝነት አቻ መሆን ችሎ ነበር፡፡ መደበኛው 90 ደቂቃ በአቻ ውጤት ተጠናቆ በጭማሪ ደቂቃው አስቻለው ግርማ ከመስመር የተሸገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ግብ አስቆጥሮ ሀዋሳ ከተማን ባለድል አድርጓል፡፡

image-9f37c1bd427ab90b5efa4de33da8ab9a4f091dfd038302d783ef94f2301e37a8-V

ጨዋታውን የመሩት አርቢቴር ዘካርያስ ግርማ 8 የማስጠንቀቅያ ካርዶችን የመዘዙ ሲሆን የሁለተኛውን ግብ አመቻችቶ ያቀበለው ደስታ ዮሃንስ ማልያው አውልቆ ደስታውን በመግለፁ በ2ኛ ቢጫ ከሜዳ ተወግዷል፡፡
አርቢቴር ዘካርያስ በመጀመርያዎቹ 20 ደቂቃዎች በርካታ ቢጫ ካርዶችን በመምዘዝ ጨዋታው መረጋጋት እንዳይታይበት ከማድረግ ይልቅ አንዳንድ ጥፋቶችን በምክር ቢያልፉ ይመረጥ ነበር በሚል ሁለቱም ክለቦች በተለይም ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅሬታ አሰምተዋል፡፡

ውጤቱ ሀዋሳ ከተማን በ16 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ ላይ ሲያስቀምጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ቢደርስበትም የደረጃ ሰንጠረዡን አዳማ ከተማን በግብ ልዩነት በልጦ ከመምራት አላገደውም፡፡

ይርጋለም ላይ ሲዳማ ቡና ዳሽን ቢራን አስተናግዶ 1-1 ተለያይቷል፡፡ ሲዳማ ቡና በኤሪክ ሙራንዳ የ6ኛ ደቂቃ ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ዳሽን ቢራ ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ቋሚ አሰላለፍ በተመለሰው የተሸ ግዛው አማካኝነት በ37ኛው ደቂቃ አቻ ሆነዋል፡፡ ጨዋታው እምብዛም የግብ ሙከራዎች ያልታዩበት ሲሆን በዝናብ በታጀበው ሁለተኛ አጋማሽ ዳሽን ቢራ የተሻለ እንቅስቃሴ አድርጓል፡፡

በውጤቱ መሰረት ዳሽን ቢራ አንድ ደረጃ በማሻሻል 13ኛ ደረጃውን ለመከላከያ ሲያስረክብ ሲዳማ ቡና በ19 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ረግቷል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

newwwwwww

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

mjnhdvsjpjf

ሌሎች የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው:-

እሁድ የካቲት 27 ቀን 2008

09፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ (ድሬዳዋ)

09፡00 ሀድያ ሆሳዕና ከ ደደቢት (ሆሳዕና)

ማክሰኞ የካቲት 29 ቀን 2008

09፡00 ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ቦዲቲ)

09፡00 መከላከያ ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)

11፡30 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *