ከፍተኛ ሊግ ፡ ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች መቐለ ከተማ እና ድሬዳዋ ፖሊስ ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 9ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡ መቐለ ከሜዳው ውጪ ድል አድርጎ መሪነቱን ሲያጠናክር ድሬዳዋ ፖሊስ ጅማ ከተማን አሸንፎ ደረጃውን አሻሽሏል፡፡

በምድብ ሀ በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍ ያለ ቦታ ላይ የሚገኙትን መቐለ ከተማ እና አአ ፖሊስን ያገናኘው የአበበ ቢቂላ ፍልሚያ በመቐለ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የደረጃ ሰንጠረዡንም በ20 ነጥብ መምራቱን ቀጥሏል፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ በአባይነህ ፌኖ ግብ ቀዳሚ ሆኖ የመጀመርያውን አጋማሽ ማጠናቀቅ ቢችልም አምበሉ ሃይሉ ገብረየሱስ መቐለ አቻ አድርጓል፡፡ በመልሶ ማጥቃት በረጅሙ የተላከውን ኳስ ለመመከት ከግብ ክልሉ የወጣው የአአ ፖሊሱ ግብ ጠባቂ ሚልዮን ኳስ በእጁ በማስቀረቱ በቀጥታ ቀይ ካርድ የተሰናበተ ሲሆን የተሰጠውን ቅጣት ምት በሱፍቃድ ነጋሽ አስቆጥሮ ጨዋታው በመቐለ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጨዋታው በርካታ አወዛጋቢ ክስተቶችን ያስተናገደ ሲሆን መቐለ ከተማ ግብ አስቆጥሮ ከጨዋታ ውጪ ተብሎ መሻሩ ፣ በሱፍቃድ ያስቆጠረው የቅጣት ምት መረብ ቀዶ መውጣቱ ፣ እልህ የተቀላቀለበት አጨዋወት ፣ በጨዋታው መጠናቀቅያ ደቂቃዎች በሁለቱ ተጫዋቾች መካከል የተከሰተው ግርግር እና በርካታ ደቂቃዎች በግርግር ባክነው ጥቂት ደቂቃዎች መጨመሩ በጨዋታው ውዝግብ ካስነሱ ክስተቶች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በምድብ ለ ነገ ሊደረግ ፕሮግራም የወጣለት የድሬዳዋ ፖሊስ እና የጅማ ከተማ ጨዋታ ሜዳው ነገ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሚደረግበት በመሆኑ ዛሬ የተደረገ ሲሆን ድሬዳዋ ፖሊስ 3-1 አሸንፏል፡፡ ደረጃውንም በከፍተኛ ሁኔታ አሻሽሏል፡፡

ሚካኤል ደምሴ እና ሊቁ አልታየ ከእረፍት በፊት ድሬዳዋ ፖሊስ 2-0 እንዲመራ ያስቻሉ ግቦች ሲያስቆጥሩ ተቀይሮ የገባው ኢዩኤል ሳሙኤል የድሬዳዋን ሶስተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ድሉ ድሬዳዋ ፖሊስን ወደ 4ኛ ደረጃ ከፍ ሲያደርገው በተከታታይ ሽንፈት እያስተናገደ የሚገኘው ጅማ ከተማ ቁልቁል መጓዙን ቀጥሏል፡፡

image-de4f65ee6b64ece7b4da02627280aac2fd9b60fb3410b66e926be264b2abc9f0-V

የዚህ ሳምንት ሌሎች ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው

ምድብ ሀ

እሁድ የካቲት 28 ቀን 2008

09:00 ሰበታ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ (ሰበታ)

09:00 ቡራዩ ከተማ ከ ሱሉልታ ከተማ (ቡራዩ)

09:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ሙገር ሲሚንቶ (መድን ሜዳ)

09:00 ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ ውሃ ስፖርት (አዲግራት)

09:00 አማራ ውሃ ስራ ከ ወሎ ኮምቦልቻ (ባህርዳር)

09:00 ወልድያ ከ ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን (መልካቆሌ)

09:00 አክሱም ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ (አክሱም)

A

ምድብ ለ

እሁድ የካቲት 28 ቀን 2008

07:00 ፌዴራል ፖሊስ ከ ሻሸመኔ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

09:00 ጅማ አባ ቡና ከ ናሽናል ሴሚንት (ጅማ)

09:00 ሀላባ ከተማ ከ ባቱ ከተማ (ሀላባ)

09:00 ነገሌ ቦረና ከ ጅንካ ከተማ (ነገሌ ቦረና)

09:00 አአ ዩኒቨርሲቲ ከ ነቀምት ከተማ (አበበ ቢቂላ)

09:00 አርሲ ነገሌ ከ አአ ከተማ (አርሲ ነገሌ)

09:00 ወራቤ ከተማ ከ ደቡብ ፖሊስ (ወራቤ)

B

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *