ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ : ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ድሬዳዋ ከተማ 0-0 አርባምንጭ ከተማ

ሀዲያ ሆሳዕና 1-3 ደደቢት (72′ ዱላ ሙላቱ 23′ 48′ ዳዊት ፍቃዱ ፣ 36′ አየለ ተስፋዬ (በራሱ ግብ ላይ)


ተጠናቀቀ!

ጨዋታው ካለግብ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

85′ ጨዋታው እንደመጀመርያው አጋማሽ ሁሉ የተቀዛቀዘ እና የግብ ሙከራዎች የማይታዩበት ሆኗል፡፡

73′ ረመዳን ናስር ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ በግቡ አግዳሚ ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

64′ የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ

ፍቃዱ ታደሰ ወጥቶ ረመዳን ናስር ገብቷል

59′ አርባምንጭ ከተማ የጨዋውን የመጀመርያው የግብ ሙከራ በተመስገብ ዱባ አማካኝነት አድርጓል፡፡

ተጠናቀቀ

ደደቢት ሀዲያ ሆሳዕናን 3-1 አሸንፏል፡፡

64′ የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ

ዳዊት እስጢፋኖ ወጥቶ ከሊፍ መሃመድ ገብቷል

52′ የተጫዋች ቅያሪ – ድሬዳዋ ከተማ

አክሌስያ ግርማ ወጥቶ ፍቃዱ ወርቁ ገብቷል

ተጀመረ

በድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል የሚደደረገው ጨዋታ 2ኛ አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ቅያሪ – አርምንጭ ከተማ

በረከት ደሙ ወጥቶ ተመስገን ዱባ ገብቷል፡፡

72′ ጎልልል!!! ሀዲያ ሆሳዕና

ዱላ ሙላቱ ለሀዲያ ሆሳዕና አስቆጥሯል፡፡ 1-3

ተጠናቀቀ!

በድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ጨዋታ የመጀመርያው አጋማሽ ካለግብ ተጠናቋል፡፡

40‘ ሄኖክ አዱኛ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ አንተነህ መሳ ይዞበታል፡፡

35′ ከፍተኛ ሙቀት እያስተናገደች ባለችው ድሬዳዋ የድሬዳዋ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ ቀዝቀዝ ያለ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡ ከአክሌሲያስ ግርማ በቀር ይ ነው ተብሎ የሚጠቀስ የግብ ሙከራም አልታየም፡፡

48′ ጎልልል!!! ደደቢት

ዳዊት ፍቃዱ የሃዲያን የጨዋታ ውጪ መስመር ጥሶ በማምለጥ ግብ ጠባቂውን ጭምር አልፎ የደደቢትን ሶስተኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ተጀመረ

በሀዲያ ሆሳዕና እና ደደቢት መካከልየሚደረገው ጨዋታ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

19′ ሱራፌል ዳንኤል ጥሩ አድርጎ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ አክሌስያ አገባው ተብሎ ሲጠበቅ በግቡ አናት ወደ ላይ ሰዶታል፡፡

ተጠናቀቀ!

የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 2-0 ተጠናቋል፡፡

45′ ሆሳእና ላይ 2 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

ተጀመረ

ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጀምሯል፡፡

36′ ጎልልል!!! ደደቢት

ሳኑሚ የመታውን ኳስ ጃክሰን ፊጣ ሲመልሰው አየለ ተስፋዬን ነክቶ ግብ ሆኗል፡፡ 0-2

23′ ጎልልል!!! ደደቢት

ዳዊት ፍቃዱ ከርቀት አክርሮ የመታው ኳስ የጃክሰን ፊጣ መረብ ላይ አርፏል፡፡ ሀዲያ ሆሳዕና 0-1 ደደቢት

ተጀመረ

1′ የሀዲያ ሆሳዕና እና ደደቢት ጨዋታ ተጀምሯል፡፡ በተጫዋች ተገቢነት ዙርያ ውዝግብ በመፈጠሩ ጨዋታው መጀመር ከነበረበት 23 ደቂቃ ዘግይቶ ተጀምሯል፡፡


የድሬዳዋ ከተማ አሰላለፍ

ሳምሶን አሰፋ

ሄኖክ አዱኛ – ሽመልስ አበበ – ብርሃኑ ሆራ – አብዱልፈታህ ከማል

ዳዊት እስጢፋኖስ – ይሁን እንዳሻው – ዮናስ ገረመው

አክሌስያ ግርማ – ፍቃዱ ታደሰ – ሱራፌል


የአርባምንጭ ከተማ አሰላለፍ

አንተነህ መሳ ታገል አበበ – አበበ ፀጋዬ – በረከት ቦጋለ – ወርቅታደል አበበ

በረከት ደሙ – ምንተስኖት አበራ – አማኑኤል ጎበና – ትርታዬ ደመቀ

ታደለ መንገሻ – በረከት ወልደፃድቅ


የደደቢት አሰላለፍ

ታሪክ ጌትነት

ስዩም ተስፋዬ – አይናለም ሃይለ – አክሊሉ አየነው – ተካልኝ ደጀኔ

ሽመክት ጉግሳ – ሄኖክ ካሳሁን – ሳምሶን ጥላሁን – ብርሃኑ ቦጋለ

ዳዊት ፍቃዱ – ሳሙኤል ሳኑሚ


የሀዲያ ሆሳዕና አሰላለፍ

ጃክሰን ፊጣ

ታረቀኝ ጥበቡ – ንጋቱ ዱሬ – ቢንያም ገመቹ – ሄኖክ አርፊጮ

አምራላ ደልቻታ – አድናን ቃሲም – አየለ ተስፋዬ – አበባየሁ ዮሃንስ – ዱላ ሙላቱ

እንዳለ ከበደ


በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለቴ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት የምናስተላልፍላችሁ ሲሆን የሀዲያ ሆሳዕና እና ደደቢት ጨዋታን በመሃል በመሃል እናደርሳችኋለን፡፡ አብራችሁን ቆዩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *