የካፍ ኮንፌድሬሽንስ ካፕ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የአፍሪካ ከተሞች ተካሂደዋል፡፡ ኡመድ ኡኩሪ ተቀያሬ ወንበር ላይ በነበረበት ጨዋታ የግብፁ ኢኤንፒፒኤ የኮትዲቯርሩን አፍሪካ ስፖርትስ ዲ አቢጃን ከሜዳው ውጪ 2-0 በማሸነፍ የማለፈ ተስፋው አስፍቷል፡፡ የአዲስ ህንፃ ክለብ የሆነው ሱዳኑ አል አሃሊ ሸንዲ በዲ.ሪ. ኮንጎው ክለብ ሴንት ኢሎኢ ሉፖፖ 2-1 ተሸንፏል፡፡ የታንዛኒያው አዛም ባልተጠበቀ መልኩ የደቡብ አፍሪካውን ቤድቬስት ዊትስን ጆሃንስርግ ላይ 3-0 መርታት ችሏል፡፡ የሊቢያው አል ኢቲሃድ ትሪፖሊ የጋናውን ሚዲአማን 1-0 አሸንፋል፡፡
አቢጃን ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢኤንፒፒአይ ከሜዳው ውጪ አፍሪካ ስፖረትስ 2-0 አሸንፏል፡፡ ካሜሮራዊው ላማ ኮኔ እና መሃሙድ ካዉድ ግቦቹን በመልሶ ማጥቃት አስቆጥረዋል፡፡ ኡመድ ኡኩሪ በጨዋታው ላይ አልተሰለፈም፡፡ ኢትዮጵያዊው አማካይ አዲስ ህንፃ በተሰለፈበት ጨዋታ አል አሃሊ ሸንዲ በሴንት ኢሎኢ ሉፖፖ 2-1 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የዩጋንዳው ኤስሲ ቪላ የዛንዚባሩን ጄኬዮ 4-0 በሆነ ሰፊ ውጤት ካምፓላ ላይ አሸንፏል፡፡ አዲስ ፈራሚው ማይክ ናዲራ፣ ማይክ ሴሩማጋ፣ ኡመር ካሱምባ እና የጨዋታው ኮከብ የነበረው ጎድፍሬ ሎዊሲባዋ ከመረብ አዋህደዋል፡፡
ቤድቬስት ዊትስ በአዛም የ3-0 አስደንጋጭ ሽንፈትን ቀምሷል፡፡ የዊትሱ አሰልጠኝ ጋቭን ሃንት በአመዛኙ ተጠባባቂ ተጫዋቾቻቸውን ማሰለፋቸው ለሽንፈት ዳርጓቸዋል፡፡ የአዛም ሶስቱም ግቦች በ10 ደቂቃው ውስጥ በሁለተኛው አጋማሽ ተቆጥረዋል፡፡ አቡበከር ሳሉም፣ ሾማሩ ካፖምቤ እና ጆን ቦኮ ሶስቱን ግቦች በስማቸው አስመዝግበዋል፡፡
ሊቢያ ባለው ያለመረጋጋት ምክንያት በሴፋክ ከተማ ቱኒዚያ ላይ አል ኢቲሃድ ትሪፖሊ ሚዲአማን 1-0 አሸንፏል፡፡ መንሱር አል-ቦርኪ ለትሪፖሊውን ክለብ ብቸኛ ግብ አስቆጥራል፡፡ መከላከያን ጥሎ ወደ አንደኛው ዙር ያለፈው የግብፁ ምስር አል-ማቃሳ የዲ.ሪ. ኮንጎው ዶን ቦስኮ በፋዩም ስታዲየም 3-1 አሸንፏል፡፡
የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ውጤቶች
ዩኤምኤስ ደ ሎም (ካሜሮን) 1-1 ኤፍዩኤስ ራባት (ሞሮኮ)
ቪ ክለብ ሞካንዳ (ኮንጎ ብራዛቪል) 0-0 ፖሊስ (ሩዋንዳ)
ሳግራዳ ኤስፕራንሳ (አንጎላ) 1-0 ሊጋ ዲፖርቲቫ ማፑቶ (ሞዛምቢክ)
ኤምሲ ኦራን (አልጄሪያ) 2-0 ስፖርቲንግ ጋግኖአ (ኮትዲቯር)
ካውካብ አትሌቲክ (ሞሮኮ) 3-0 ባራክ ያንግ ኮትሮለርስ (ላይቤሪያ)
ቤድቬስት ዊትስ (ደቡብ አፍሪካ) 0-3 አዛም (ታንዛኒያ)
ሬኔሳንስ (ቻድ) 0-2 ኤስፔራንስ ቱኒዝ (ቱኒዚያ)
ሃራሬ ሲቲ (ዚምባቡዌ) 1-2 ዛናኮ (ዛምቢያ)
ስታደ ጋቢሲን (ቱኒዚያ) 2-1 ካሎም ስታር (ጊኒ)
ምስራ አል-ማቃሳ (ግብፅ) 3-1 ዶን ቦስኮ (ዲ.ሪ. ኮንጎ)
አትሌቲኮ (ቡሩንዲ) 0-2 ሲኤፍ ሞናና (ጋቦን)
አፍሪካ ስፖርትስ (ኮትዲቯር) 0-2 ኢኤንፒፒአይ (ግብፅ)
ናሳራዋ ዩናይትድ (ናይጄሪያ) 1-0 ሲኤስ ኮንስታንታይን (አልጄሪያ)
ሴንት ኢሎኢ ሉፖፖ (ዲ.ሪ. ኮንጎ) 2-1 አል አሃሊ ሸንዲ (ሱዳን)
ኤስሲ ቪላ (ዩጋንዳ) 4-0 ጄኬዩ (ዛንዚባር)
አል-ኢቲሃድ ትሪፖሊ (ሊቢያ) 1-0 ሚዲአማ (ጋና)