ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ መከላከያ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 0-0 መከላከያ

ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት በሶከር ኢትዮጵያ

ተጠናቀቀ!
ጨዋታው ሳቢ እንቅስቃሴ ሳይታይበት እንዲሁም በርካታ የግብ ሙከራ ሳያስተናግድ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቆ 3 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

89′ ጋብሬል አህመድ ከርቀት የመታዉ ኳስ ኢላማዉን ስቶ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

79′ እንደ መጀመሪያዉ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ወደ ግብ በመድረስ ረገድ ደከም ያሉ ሲሆን በአንፃራዊነት መከላከያዎች የተሻለ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡

64′ ኤፍሬም አሻሞ ከመስመር እየገፋ ወደ መሀል በመግባት የሞከረዉ ኳስ ለጥቂት መረቡን ታኮ ወደ ዉጭ ወጥቷል፡፡

49′ መሉአለም ጥላሁን ከፍሬው ሰለሞን ያገኘዉን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ግብ ጠባቂዉ ፌቮ አዉጥቶበታል፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
– – – – –

እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ ካለ ግብ ተጠናቋል፡፡

45′ መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

40′ ሙሉአለም ጥላሁን ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የቅጣት ምት ሳሙኤል ሳሊሶ ቢመታውም አማካኝነት ግብ ጠባቂዉ ፌሾ ኢማኑኤል ይዞታበል፡፡

30′ ቢኒያም አሰፋ በግል ጥረቱ ያገኘነውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮ ለጥቂት ወደ ዉጭ ወጥቶበታል፡፡

15′ ሁለቱም ቡድኖች ኳስን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ ቢያሳዩም ወደ ጎል በመድረስ ረገድ ግን ቀዝቀዝ ያሉ ናቸው፡፡

1′ ጨዋታው ተጀምሯል

*የሁለቱ ቡድኖች ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ገብተው ሰላምታ እየተለዋወጡ ይገኛሉ

————–
የመከላከያ አሰላለፍ
ጀማል ጣሰው
ነጂብ ሳኒ – አዲሱ ተስፋዬ – ሙሉቀን ደሳለኝ – ቴዎድሮስ በቀለ
ሚካኤል ደስታ – በሃይሉ ግርማ – ፍሬው ሰለሞን – ሳሙኤል ሳሊሶ
ሙሉአለም ጥላሁን – መሃመድ ናስር
————-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ
ኢማኑኤል ፌቨር
ዳንኤል አድሃኖም – ቢንያም ሲራጅ – አቤል አበበ – አንተነህ ገብረክርስቶስ
ጋብሬል መሃመድ – ሰለሞን ገብረመድህን
ኤፍሬም አሻሞ – ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን – ቢንያም በላይ
ቢንያም አሰፋ

 

–      –        –       –        –        

ሰላም!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታ ዛሬከ11:30 ጀምሮ በአአ ስታድየም ይካሄዳል፡፡

ሶከር ኢትዮጵያም ይህንን ጨዋታ በቀጥታ ከአአ ስታድየም በፅሁፍ ታደርሳችኋለች፡፡

መልካም ቆይታ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *