የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ፡ ኢትዮጵያ ከ አልጄርያ – ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ኢትዮጵያ 1-1 አልጄርያ
[ድምር ውጤት 1-2]
ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር ኢትዮጵያ

– – – –
ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ አልጄርያም በድምር ውጤት ተከታዩን ዙር ተቀላቅላለች፡፡

90′ መደበኛው ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃዎች ተጨምረዋል፡፡

ጎልልል!!!
86′ ዴሊላ ዜሮኪ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ በግንባሯ በመግጨት የአልጄርያን ወሳኝ ግብ አስቆጥራለች፡፡

84′ ኢትዮጵያ ጫና ፈጥራ መጫወት ብትችልም አስደንጋጭ የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻለችም፡፡

78′ ሀቢባ ከረጅም ርቀት የሞከረችው ኳስ ኢላማውን ስቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

73′ ከመስመር የተሻገረውን ኳስ ረሂማ ዘርጋ ጨርፋ ለሽታዬ ብታመቻችላትም ግብ ጠባቂዋ ደርሳ ይዛባታለች፡፡

70′ ቤንላዛር የመታችው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

69′ ቢጫ ካርድ
ጥሩአንቺ በፍፁም ቅጣትምት ክልል ጠርዝ በሰራችው ጥፋት የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

61′ ቢጫ ካርድ
እፀገነት ብዙነህ ሀቢባ ላይ በሰራችው ጥፋት የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

57′ ሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመርያው የወረደ እንቅስቃሴ እየታየበት ይገኛል፡፡ ሁለቱም የግብ እድል ለመፍጠር የሚያደረጉት ጥረትም አናሳ ነው፡፡

51′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ዳግማዊት ብታወጣውም የተመለሰውን ኳስ ቤንላዛር ሞክራ ሀብታም እሸቱ ከመስመር ላይ አውጥታዋለች፡፡

ተጀመረ!
ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል፡፡
– – – – – –

እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በኢትዮጵያ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45+1 ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ እፀገነት ሞክራ ተደርቦ ወጥቶባታል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ መደበኛ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 1 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

43′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ከግቡ በኋላ የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

34′ ጎልልልልል!!!!
ህይወት ከቅጣት ምት ያሻገረችውን ኳስ ፌውዶል ስትመልሰው በቅርብ ርቀት የነበረችው ሎዛ ወደ ግብነት ቀይራለች፡፡

33′ ቢጫ ካርድ
ሀቢባ ሳዶ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

33′ ዴሊላ ዜሮኪ ከመስመር ወደ መሃል በማጥበብ የሞከረችውን ኳስ ዴ፤ግማዊት በቀላሉ ይዛዋለች፡፡

31′ ሎዛ አበራ ከቅጣት ምት የሞከረችው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

29′ ከማዕዘን የተሻማውን ኳስ ዴሊላ ዜሮኪ በግንባሯ ገጭታ ብትሞክርም ብርቱካን ከግቡ መስመር አውጥታዋለች፡፡

28′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች የተረጋጋ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻሉም፡፡

ቢጫ ካርድ
24′ ሽታዬ ሲሳይ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ጥፋት ሳይሰራባት ወድቃለች በሚል የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክታለች፡፡

21′ ከማዕዘን ምት የተሻማውን ኳስ ጥሩአንቺ ሞክራ የአልጄሪያ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል፡፡

18′ የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ከጨዋታ ውጪ በመግባት ላይ ይገኛሉ፡፡

11′ ሽታዬ ሲሳይ ከርቀት የመታችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ ፌዶውል ይዛባታለች፡፡

10′ ከቅጣት ምት የተሻገረውን ኳስ ቤንላዛር ሞክራ ወደ ውጪ ወጥቶባታል፡፡

5′ የተሻማውን የማእዘን ምት ጥሩአንቺ ሞክራ ናጄት ፌዶውል አድናዋለች፡፡ የተመለሰውን ኳስ ረሂማ ሞክራ በድጋሚ ስትመልስ እንደገና ሀብታም ሞክራ ለሶስተኛ ጊዜ አድናለች፡፡

4′ ሎዛ አበራ የሞከረችውን ኳስ ግብ ጠባቂዋ አውጥታዋለች

1′
ተጀመረ

09፡45 ተጫዋቾቹ አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

09:30 የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች ሜዳ ገብተው ሰውነታቸውን እያፍታቱ ይገኛሉ፡፡

የኢትዮጵያ አሰላለፍ (4-3-3)

ዳግማዊት መኮንን

18.ሀብታም እሸቱ – 4.ጥሩአንቺ መንገሻ – 5.ፅዮን እስጢፋኖስ – 17.እፀገነት ብዙነህ

11.ብርቱካን ገብረክርስቶስ (አ) – 14.ህይወት ደንጊሶ – 16.ብሩክታዊት ግርማ

9.ረሂማ ዘርጋ – 7.ሎዛ አበራ – 10.ሽታዬ ሲሳይ

ተጠባባቂዎች
ንግስት መአዛ ፣ ፋሲካ በቀለ ፣ መስከረም ኮንካ ፣ አዲስ ንጉሴ ፣ ቅድስት ቦጋለ ፣ ኤደን ሽፈራው ፣ መዲና አወል
አሰልጣኝ – ብርሃኑ ግዛው
– – – – – –
የአልጄርያ አሰላለፍ
የአልጄርያ አሰላለፍ (4-4-2)
16.ናጄት ፈዱል
11.ሜሳዎር ፋይዛ – 5.ባራ ፋቲማ – 22. አርቢ ኢስማ – 4.ሴኮአን ፋቲማ (አ)
14.ቤንላዛር ሚርያም – 10.ሳዶ ሀቢባ – 17.ሰብሪና ኦመር – 19.ነኢማ ቦሂኒ
15. ፈቲያ ባኬዳ – 12.ዳሊላ ዜሮኪ

ተጠባባቂ
1.ታክኒት ካሂና ፣ 6. ያስሚን ቦውፍራ ፣ 7. ላቲታ አክሊ 2. ሆርያ አፋክ ፣ 8.ሰሚራ ተቢ 13. ሆርያ ሴድራቲ ፣ 9. ኢሜኒ ሜሮሽ
አሰልጣኝ – አዘዲን ቺህ
– – – – –

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *