ፀጋአብ ግዛው ወደ አሳዳጊው ቤት ተመልሷል

ፀጋአብ ግዛው ወደ አሳዳጊው ቤት ተመልሷል

በዝውውሩ የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የመስመር ተከላካዩን ለማስፈረም ተስማምተዋል።

ከሰሞኑ ወደ ዝውውሩ በመግባት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው እየቀላቀሉ የሚገኙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በሀዲያ ሆሳዕና በግሉ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈውን ሁለገቡን ተጫዋች ፀጋአብ ግዛውን ለማስፈረም መቃረባቸው ታውቋል።

በቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን አጥቂ በመሆን ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ አሳይቶ የነበረው ፀጋአብ በኋላም ወደ ሀዲያ በማቅናት ባለፉት ሁለት ዓመታት ቆይታ ያደረገ ሲሆን በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለቡድኑ በሠላሳ ሰባት ጨዋታዎች ላይ 3266 ደቂቃዎችን ተሳትፏል። አሁን ዳግም ወደ አሳዳጊ ቤቱ ለመጫወት የሁለት ዓመት ስምምነት አድርጓል።