የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስባቸውን ይፋ አደረጉ

ሱዳን ስብስቧን ይፋ ስታደርግ’ሀዋክያን’ የተባሉትም በተደረገው ጥረት ዳግም ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያገለግሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል

ሦስት ጎረቤት ሀገራት በጣምራ ለሚያዘጋጁት
የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ የተደለደለችው እና በምድብ ማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹን የምትገጥመው ሱዳን ስብስቧ ይፋ አደርጋለች።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ጋናዊው ጄምስ ክዌሲ አፒያህ ከኢትዮጵያ እና ሞዛምቢክ ጋር ለሚደርጓቸው ጨዋታዎች 33 ተጫዋቾች የያዘው ስብስብ ይፋ ሲያደርጉ ከሀገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር በፈጠሩት ቁርሾ ብሔራዊ ቡድኑን እንዳያገለግሉ ታግደው የነበሩ ተጫዋቾችም በአሰልጣኙ ጥረት ዳግም ብሔራዊ ቡድኑን እንዲያገለግሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

በአረብ ዋንጫ እና አፍሪካ ዋንጫ ላይ በርከት ያሉ ተጫዋቾች በጉርሻ እና በክፍያ ጉዳይ ላይ ከፌደሬሽኑ ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ ገብተው የነበረ ሲሆን ፌደሬሽኑም ሁከት ፈጥረዋል ላላቸው ተጫዋቾች ከቡድኑ ታግደው ዳግም ጥሪ እንዳይደረግላቸው የሚከለክል አቋም ይዞ ነበር።

የ66 ዓመቱ ጋናዊው አሰልጣኝ ፌደሬሽኑ የያዘው አቋም ነገሮች አስቸጋሪ እንዳረገበት በመግለፅ ባደረገው ውይይት እግድ የተላለፈባቸው ተጫዋቾች ዳግም ወደ ስብስቡ የቀላቀለ ሲሆን ለረዥም ጊዜያት ጉዳት ላይ የነበረው የቡድኑ አምበል ረመዳን አጋብም ጥሪ ተደርጎለታል።