ከዋልያዎቹ ስብስብ አንድ ተጫዋች ወደ መዲናዋ ከተማ ተመልሷል

ከዋልያዎቹ ስብስብ አንድ ተጫዋች ወደ መዲናዋ ከተማ ተመልሷል

ሀዋሳ ላይ ዝግጅቱን እያደረገ ካለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ አንድ ተጫዋች በጉዳት ወጥቷል።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በመስከረም ወር ከሱዳን እና ከሴኔጋል ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ሲያደርግ ከነበረውን ዝግጅት አሁን ወደ ሀዋሳ በማቅናት እየሰራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ የመቻሉ ተከላካይ ግሩም ሀጎስ በጉዳት ምክንያት ከሀዋሳ ወጥቶ ወደ አዲስ አበባ መመለሱን ሰምተናል።

አስቀድመን ባደረስናችሁ መረጃ መሰረት ግሩም ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ያስተናገደ ሲሆን በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ህክምናውን እንደሚከታተል የሰማን ሲሆን ከጉዳቱ ሁኔታ አንፃር ለሳምንታት ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል አውቀናል።