ሁለቱ የዋልያዎቹ ተጫዋቾች በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ

ከቀናት በፊት ባደረስናቹህ መረጃ መሠረት በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ የሚገኙ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ፀጋአብ ግዛው እና የመቻሉ ግሩም ሐጎስ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ተነጥለው ለብቻቸው ልምምድ ሲሰሩ እንደነበረ መግለፃችን ይታወሳል።
ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባደረገቸው ማጣራት በዚህ ክረምቱ ወደ እናት ክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተመለሰው ፀጋአብ ግዛው ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሙሉ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን የመቻሉ ተከላካይ ግሩም ሐጎስ ግን እስካሁን ድረስ ወደ ልምምድ እንዳልተመለሰ አረጋግጠናል። ላለፉት ስድስት ቀናት ልምምድ ያልሰራው ተጫዋቹ ከቡድኑ ጋር ወደ ሀዋሳ ቢያቀናም ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ልምምድ እንዳልተመለሰ ታውቋል።

