የኢትዮጵያ እና አልጄርያ ብሄራዊ ቡድኖች ዛሬ አአ ገብተዋል

የኢትዮጵያ እና አልጄርያ ብሄራዊ ቡድኖች የምድባቸው 4ኛ ጨዋታን ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ዋልያዎቹ ከ7-1 ሽንፈት ማግስት (ቅዳሜ) ቀትር ላይ ከአልጀስ በመነሳት ማምሻውን ግብጽ ካይሮ ሲደርሱ ከ8 ሰአት የካይሮ ትራንዚት በኀላ አጭር በረራ በማድረግ ጠዋት 1:30 ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የአልጄርያ ብሄራዊ ቡድን በበኩሉ ዛሬ ከአልጀርስ በመነሳት በቀጥታ በረራ ከደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ደርሷል፡፡

“ለ ፌኔስ” ተጫዋቾችን ፣ አሰልጣኝ እና የህክምና ባለሙያዎችን እንዲሁም ጋዜጠኞችን ጨምሮ 56 የልኡካን ቡድን በመያዝ በቻርተርድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ሲደርሱ በፌዴሬሽኑ ሃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ጨዋታው ማክሰኞ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ሲደረግ ከአልጄርያ ጋር በተመሳሳይ ሰአት አአ የገቡት ኬንያውያን ዳኞች ጨዋታውን ይመሩታል፡፡

ምድብ 10ን አልጄርያ ከ3 ጨዋታ ሙሉ 9 ነጥብ በመያዝ ስትመራ ኢትዮጵያ ትላንት ሌሶቶን 2-0 ካሸነፈችው ሲሸልስ ጋር በተመሳሳይ 4 ነጥብ በእርስ በእርስ ውጤት ቀድማ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ሌሶቶ ካለምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *