ቢንያም በላይ ለኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ቡድን ሲጠራ 5 ተጫዋቾች ተቀንሰዋል

የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን 5 ተጫዋቾችን በእድሜ ጉዳይ ከቡድኑ ሲቀንስ ተጨማሪ ተጫዋች ለማካተት ጥሪ ማድረግ መጀመሩ ታውቋል፡፡ 

ከቡድኑ የተቀነሱት ተጫዋቾች ከ20 አመት በታች ቡድኑ ከሶማልያ ባደረገው ጨዋታ የመጀመርያ ተሰላፊ የነበሩት እያሱ ታምሩ እና በሱፍቃድ ነጋሽ ፣ በሁለተኛው አጋማሽ ተቀይሮ ገብቶ ጨዋታ ያደረገው ከነአን ማርክነህ እንዲሁም አምና ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን አባል የነበሩት ክብረአብ ዳዊት እና ማርዋን ራያ ናቸው፡፡

አሰልጣኝ ግርማ ሀብተዮሃንስ እና ረዳቶቻቸው በተቀነሱት ተጫዋቾች ምትክ ተጫዋቾች መጥራት የጀመሩ ሲሆን የብሄራዊ ቡድኑ ተጫዋች ቢንያም በላይ ቡድኑን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር በቻን ፣ ሴካፋ እና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያዎች ተሳትፎ ያደረገው ቢንያም በላይ እሁድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲዳማ ቡና ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ላይ ተሳትፎ ሰኞ ከ20 አመት በታች ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከቢንያም በላይ ተጨማሪ ከቡድኑ ጋር ዝግጅት ላይ ሲሳተፍ ቆይቶ በመጨረሻ ከሶማልያው ጨዋታ ውጪ የሆነው ዘሪሁን ብርሃኑ ወደ ቡድኑ ተመልሷል፡፡

ቡድኑ ሌሎች አዳዲስ ተጫዋች ከተለያዩ ክለቦች ጥሪ እያቀረበ እንደሆነ የታወቀ ሲሆን በዝግጅት ላይ ታይተው ለቡድኑ ይመጥናሉ የሚባሉ ተጫዋቾች ይያዛሉ ተብሏል፡፡

PicsArt_1460055123689

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *