የኢትዮጵያ እግርኳስ ባለውለታዎች መታሰቢያ ውድድር ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ዛሬ ረፋድ በተሰጠ መግለጫ ከጤና ቡድኖች ሕብረት አዘጋጆች አንዱ የሆነው የኢትዮ አፍሪካንስ ተወካዩ ሚካኤል ታደለ ይህንን ውድድር ያዘጋጁበት ዓላማ የጤና ቡድኖች ሕብረት የጤና እንቅስቃሴ እያደረገ የቀድሞ እግርኳስ ባለውለታዎቻችንን ለማሰብ የታቀደበት ስለመሆኑ መግለጫ ሲሰጥ ሜዳውን ያለ ክፍያ በነጻ በማመቻቸቱ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉላቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አቶ ዳዊት ላደረጉት ቀና ትብብር አመስግኗል። አቶ ሚካኤል አክሎም ወደፊት ሕብረቱ ተጠናክሮ በማኅበራዊ ሕይወት ለድጋፍ ሥራዎች እንደሚተባበር እና ውድድሩን ዓመቱን ሙሉ ለማድረግ ማቀዳቸውን ጠቁሟል። ከዚህ በፊትም ለመሸሻ ወልዴ በአራት ቡድኖች እና በ3 ጨዋታዎች ብቻ የመታሰቢያ ውድድር ይካሄድ እንደነበርም አስታውሷል።
በመቀጠልም ሌላኛው የሕብረቱ ተወካይ አቶ ፍቃዱ ተካ ይሕ ውድድር ከሁሉም ቡድኖች ጋር ውይይቶች ተደርገው የተወሰነ እንጂ በራሳችው የተወሰነ እንዳልሆነ እንዲሁም 90% የሚሆኑ ተጫዋቾች በውድድሩ በሚታሰቡ አሰልጣኞች የሰለጠኑ መሆናቸውን ሲናገሩ ውድድሩ ምንም ገቢ እንደሌለው እንዲሁም የቀድሞ የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ንጉሤ ገብሬ እና አቶ በሀብቱ የተሻለ ሀሳብ እንደሰጧቸው ገልጸው “ውድድሩ የፊታችን ረቡዕ 8 ሰዓት በሻላ ጤና ቡድን እና በኢትዮ አፍሪካን ጨዋታ ይጀመራል ፤ ለዚህ መሳካት የረዳችሁን አካላትም በኮሚቴው ስም እናመሠግናለን።” ብለዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ንጉሤ ገብሬ “ለውድድሩ መሳካት ፍቃደኛ ለሆኑት ሁሉ ምስጋናቸውን ሲያቀርቡ አቶ በሀብቱ በበኩላቸው “ውድድሩ ቀጣይነት እንዲኖረው መትጋት አለባችሁ መቋረጥ የለበትም።” ካሉ በኋላ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች በኮሚቴው ምላሽ ተሰጥቷል።
በውድድሩ 9 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን
በምድብ “ሀ”
1. ሻላ
2. አድዋ
3. ኢትዮ አፍሪካንስ
4. ፊኔክስ
5. ኢትዮጵያ ቡና
በምድብ “ለ”
1. አበበ ቢቂላ
2. ኢትዮ አዲስ
3. ኳስ ሜዳ
4. መርካቶ
ተደልድለዋል።
* ይህ ውድድር በቀጣይ ዓመታዊ ውድድር ይሆናል።
በመግለጫው መገባደጃ እንደተገለጸውም ከክለቦች መመዝገቢያ የሚሰበሰበው ገንዘብ ለሁለት ነገሮች ታስቧል። ለመታሰቢያ እና ለፍቃዱ ዶቃ ፕሮጀክት (ድሬዳዋ) መቋቋሚያ የሚሆን ገንዘብ መስጠት ነው።
የዳኞች ወጪ 4000 ፣ የጽዳት 2000 እና የፊዚዮቴራፒስት 1000 በአጠቃላይ በጨዋታ 7000 ብር ( ሌሎች ውድድር ማስኬጃ ወጪዎች ሳይጨመሩ ) ለአንድ ጨዋታ ወጪ የታሰቡ መሆናቸው ተጠቁሟል። ይህም በውድድሩ 15 ጨዋታዎች ተካሂደው ከሚወጣው ወጪ እና ለመመዝገቢያ ከሚሰበሰበው ገንዘብ ያለውን ትርፍ ነው ለፕሮጀክቱ ለመለገስ የታሰበው።
ውድድሩ የፊታችን ረቡዕ ይጀመራል።