ለአሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል  

ለአሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል  

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ተዘጋጅቶ ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የአሰልጣኞች  አቅም ማጎልበቻ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። 

አካዳሚው ዓላማ አድርጎ ከተነሳባቸው ተግባሮች ውስጥ ተወዳዳሪ እና ሀገርን የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን በማፍራት ለብሔራዊ ቡድን እና ለክለቦች ብቁ ማድረግ፤ በስፖርቱ ዘርፍ ጥናቶችን በማድረግ የመፍትሔ ሀሳቦችን ማቅረብ እና በስፖርቱ ስር ላሉ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት ዋነኛ ተልዕኮ አድርጎ እየሰራ ይገኛል።

ከነዚህም ውስጥ የአሰልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና  አንዱ እና ተጠቃሽ ሲሆን ጥሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት ብቁ የሆኑ አሰልጣኞች የሚያስፈልጉ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በአምስት የተለያዩ የስፖርት አይነቶች በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣በቮሊቦል፣ በቅርጫት ኳስ እና በወርልድ ቴኳንዶ ከሀገሪቱ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ለ175 አሰልጣኞች በዘርፉ ልምድ ባካበቱ እና በስራቸው አንቱታን ባተረፉ አሰልጣኞች አማካኝነት በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የተደገፈ ስልጠናን አሰላ በሚገኘው በአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰጥ ቆይቷል።

በመዝጊያው መርሐግብር ላይም በስልጠናው ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋና ሰርተፍኬት በመስጠት ተጠናቋል።