የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ዘላለም አባተ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል።
የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ መሪነት በፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የቋጨው ኢትዮጵያ ቡና በላይሰንስ ጉዳይ የተነሳ በቅርቡ ረዳት አሰልጣኝ የነበረውን አብይ ካሳሁንን የቡድኑ አለቃ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የመጀመሪያውን የክረምቱን ፈራሚ በእጁ ማስገባቱ ታውቋል።
አጥቂው ዘላለም አባተ ማረፊያው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል። ከአረካ ከተማ በአንደኛ ሊግ በመጫወት የክለብ ህይወትን የጀመረው የመስመር እና የፊት አጥቂው ላለፉት አምስት አመታት ደግሞ በወላይታ ድቻ ቆይታን ካደረገ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።
