በድምሩ ለአስር ዓመታት በመቻል ቤት ቆይታ የነበረው አጥቂ ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።
አሰልጣኝ ሙልጌታ ምህረትን ከሾሙ በኋላ ቡድኑን ለማጠናከር ወሳኝ ተጫዋቾችን በማስፈረም ጠንካራ ዝውውር የፈፀሙት መቻሎች ከአጥቂያቸው ምንይሉ ወንድሙ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ታውቋል።
አጥቂው ምንይሉ በመሐል ለአንድ አንድ ዓመት በወላይታ ድቻ እና በባህር ዳር ከተማ ቆይታ ካደረገበት ጊዜ ውጭ በድምሩ አስር ዓመታት አንበል በመሆን በቡድኑ ያገለገለ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡደን በተለያዮ ጊዜያት ተጫውቶ ማሳለፉ ይታወሳል።
