ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ራሱን ከዳኝነት አገለለ

ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ራሱን ከዳኝነት አገለለ

ያለፉትን ረጅም ዓመታት በወጥነት በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ መድረኮች በዳኝነት ያገለገለው በአምላክ ተሰማ ራሱን ከዳኝነት አግልሏል።

በዓለም ዋንጫ፣ የአፍሪካ ዋንጫ፣ በቻን፣ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ኮንፌሬዴሽን ዋንጫ፣ የዓለም ክለቦች ዋንጫ እና ኦሎምፒክን ጨምሮ በርካታ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ታላላቅ ጨዋታዎችን በመምራት የሀገሩን ስም ከፍ አድርጎ ያስጠራው በአምላክ ተሰማ ኢትዮጵያን በሀገር አቀፍም ሆነ በዓለም አቀፍ መድረክ በማገልገሉ ኩራት እንደሚሰማው ገልጾ ፊፋ ለሰጠው ዕድል በማመስገን ከኢንተርናሽናል ዳኝነት ራሱን ማግለሉን ለፊፋ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።