የሉሲዎቹ አጥቂ ከአንድ ዓመት የታንዛኒያ ቆይታዋ በኋላ ወደ ሞሮኮ ክለብ አቅንታለች።
የእግርኳስ ሕይወቷን በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የጀመረችው እንዲሁም በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች እና ዋናውን የሴቶች ብሔራዊ ቡድኑን ጨምሮ ለአዲስ አበባ ከተማ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተጫወተች በኋላ ማረፊያዋን የታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ አድርጋ ላለፈው አንድ ዓመት ቆይታ ያደረገችው አጥቂዋ አርያት ኦዶንግ አሁን ደግሞ በነጻ ዝውውር የሞሮኮውን “አር ኤስ ቢር ካን” ተቀላቅላለች።