የፊታችን ዓርብ ከዋልያዎቹ ጋር ፍልሚያ የሚጠብቀው የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።
የ2026 ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች በያዝነው ሳምንት መካሄድ ይጀምራሉ። ሆኖም በአፍሪካ ዞን በምድብ “1” ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ተደልድላ ካደረገቻቸቸው ስድስት ጨዋታዎች አንድ ድል ፣ ሦስት አቻ እና ሁለት ሽንፈት አስተናግዳ በ6 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን ይህንን ምድብ ደግሞ ከስድስቱ ጨዋታዎች አምስቱን አሸንፋ በአንዱ አቻ የተለያየችው እና 16 ነጥቦችን የያዘችው ግብጽ እየመራችው ትገኛለች።
ሁለቱ ብሔራዊ ቡድንች የፊታችን ዓርብ እርስ በእርስ በመፋለም የምድብ 7ኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን ፈርዖኖቹ የቡድን ስብሰባቸውን ይፋ አድርገዋል።
ለ25 ተጫዋቾች በቀረበው ጥሪ አራት ግብ ጠባቂዎች ፣ ዘጠኝ ተከላካዮች ፣ ስምንት አማካዮች እንዲሁም አራት አጥቂዎች የተካተቱ ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወቱት የሊቨርፑሉ መሐመድ ሳላህ እና የማንቸስተር ሲቲው ኦማር ማርሙሽም ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ይገኛሉ።
ሙሉ የግብጽ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ከምስሉ ጋር ተያይዟል 👇