ከግብፅ ጋር የሚደረግ ጨዋታ ትርጉም ያለው ነው

ከግብፅ ጋር የሚደረግ ጨዋታ ትርጉም ያለው ነው

👉 “ከግብፅ ጋር የሚደረግ ጨዋታ ትርጉም ያለው  ነው።”

👉 “ከባድ ጨዋታ ነው የሚጠብቀን።”

👉 “ጨዋታውን የሚሰጠንን ዓርብ ምሽት እንጠብቃለን።”

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከግብፅ ጋር ካለው ከታሪካዊ ተቀናቃኝነት አንፃር ለጨዋታው የሰጡት ግምት እንዴት እንደሆነ ለቀረበ ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ከግብፅ እና ሴራሊዮን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ አስመልክቶ ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። በመግለጫውም ለዋልያዎቹ አለቃ አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ “ከግብፅ ጋር የሚኖረው ጨዋታ ሁልጊዜ የተለየ ትኩረት አለው የታሪክ ተቀናቃኝነት ጋር ተያይዞ ምንያህል በስነ ልቦና ተዘጋጅታችኋል? በሚለው ዙርያ ” ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ

“በስነ ልቦና ተዘጋጅተናል ብዙ ተመልካች እንደሚገባ እንጠብቃለን ያንን መቋቋም ከባድ ጨዋታ ነው የሚጠብቀን። ጠንካራ ጨዋታ እንደሚሆን እናውቃለን። እኛም በዛው ልክ ተገቢውን ዝግጅት እያደረግን ቆይተናል። ሜዳ ላይ የሚሆነውን አብረን እናያለን። ጨዋታው የሚሰጠንን ዓርብ ምሽት እንጠብቃለን ትርጉም ሰጥተን ጥሩ ፉክክር ይደረግበታል ብዬ አስባለው። ከግብፅ ጋር በመሆኑ ጨዋታው ትልቅ ትርጉም አለው ብለን እናስባለን።” ብለዋል

በተጨማሪም የወላይታ ድቻ እና የኢትዮጵያ መድን የልምምድ ጨዋታ ለግብፅ ጨዋታ በቂነው ብለው ያስባሉ ? ተብለው ለተጠየቁት አሰልጣኙ ሲመልሱ “ያደረግነው የልምምድ ጨዋታ በጣም ነው የሚጠቅመን ጠንካራ እና ደካማ ጎናችንን እንድንፈትሽ አድርጓናል። ኢንተርናሽናል ጨዋታ ካለባቸው ቡድኖች ጋር በመሆኑ ጨዋታው አካል ብቃታችንን እና ታክቲካል መረዳታችንን እንድናይ በማስቻሉ ለእኛ አስፈላጊ ነበር።” ብለዋል።