👉 “ትልቅ የታሪክ አሻራ ባስቀመጥንበት የሕዳሴው ግድብ በሚመረቅበት ሰዓት የሚደረግ ጨዋታ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው። አቶ ባሕሩ ጥላሁን
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማምሻውን ወደ ግብፅ ከማቅናቱ በፊት በአሁኑ ሰዓት በጁፒተር ሆቴል አጠቃላይ የጉዞውን ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ባሕሩ ጥላሁን ከመገናኛ ብዙኀን ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከል ከግብፅ ጋር የሚደረግ ጨዋታን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚሰጠውን ትርጉም ተጠይቀው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ሲመልሱ
“ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይህ ጨዋታ ትልቅ ትርጉም ያለው ጨዋታ ነው። በተለይ ትልቅ የታሪክ አሻራ ባስቀመጥንበት የህዳሴው ግድብ በሚመረቅበት ሰዓት የሚደረግ ጨዋታ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም ያለው ጨዋታ ነው። እንዲሁም የንጋት ሐይቅ በሚሰየምበት ወቅት በመሆኑ እንደ ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽንም ሆነ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ጨዋታ ነው። ለዚህም ብሔራዊ ቡድኑ የተሻለ ነገር እንዲያደርግ ፍላጎታችን ነው። ለዚህም ይህን ብሔራዊ ቡድኑ በቀደመ መልኩ ቀደም ብሎ ወደ ዝግጅት መግባቱን እና አሰልጣኙ ባቀረበው ዕቅድ መሰረት ቡድኑ እንዲሰባሰብ እና እንዲዘጋጅ ሆኗል። ይሄም የሆነበት አንደኛ እኛ ጋር ኦፍ ሲዝን ነው። ልጆቹ ከዝግጅት አይደለም እየተሰባሰቡ ያሉት ለዚህም ቀደም ብለው እንዲጀምሩ መደረጉን ሌላው ለጨዋታው በተሰጠው ልዩ ትኩረት በመሆኑ ገልፀዋል።”
እንዲሁም ከሀገር ውስጥ የልምምድ ጨዋታ ከማድረግ ይልቅ ከጨዋታው ክብደት አንፃር በአፍሪካ በተመሳሳይ ሀገራትን በወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ለምን አልታሰበም? ለተባሉት ሲመልሱ
“አሁን ያለንበት ወቅት በፊፋ ካላንደር መሠረት ሀገራት ሁለት ወዳጅነት ጨዋታ በተከታታይ የሚያደርጉበት ጊዜ ስለሆነ በዚህ ወቅት ሀገራችንን ከአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ባለ መኖሩ እንደሆነ ይህንን ከግንዛቤ ማስገባት አለበት ብለዋል።”