የጣና ሞገዶቹ ዝግጅታቸውን በይፋ ጀምረዋል

የጣና ሞገዶቹ ዝግጅታቸውን በይፋ ጀምረዋል

የ2017 የነሀስ አሸናፊ የሆኑት ዉሃ ሰማያዊ ለባሾቹ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።


በአሰልጣኝ ደግአረገ ግዛው የሚመሩት የጣና ሞገዶች ባሳለፍነው የዉድድር ዘመን ካደረጓቸው 34 ጨዋታወች አስራ አምስት ጨዋታወችን በማሸነፍ በዘጠኙ አቻ በመውጥት በአስሩ ተሸንፈው 54 ነጥብ በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃን ይዘውበመጨረስ የነሀስ ተሸላሚ መሆን የቻሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ለቀጥዩ የውድድር አመት ያግዛቸው ዘንድ በወጣት ተጫዋቾች ቡድናቸውን እያዋቀሩ ይገኛሉ።

በክረምቱ የዝውውር መስኮትም ወደ ገበያው በመግባት ዮሐንስ ደረጄ፣ ብሩክ ሰሙ፣ ማንያዘዋል ካሳ እና አናንያ ጌታቸውን በማስፈረም የመሳይ አገኘሁ ፣ ፍቅረሚካኤል ዓለመሙ፣ አምሳሉ ሳለ፣ ግርማ ዲሳሳ፣ ይገርማል መኳንንት እና ሄኖክ ይበልጣልን ዉል አራዝመዋል። የጣና ሞገዶቹ ቀሪ የዝውውር ስራዎችን እየሰሩ ቅድመ ዝግጅታቸውን ወደ አዳማ ተጉዘው ማድረግ ጀምረዋል።