የግብፅ እና ኢትዮጵያን ፍልሚያ የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።
በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአንድ ምድብ የተደለደሉት የግብፅ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኖች በነገው ዕለት በካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየን ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ሲሆን የሀገራችን ብሔራዊ ቡድንም ከትናንት በስትያ ወደ ስፍራው ማቅናቱ ይታወቃል። ነገ ምሽት 4 ሰዓት የሚደረገውን የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታንም የሚመሩ አልቢትሮሽ እነማን እንደሆነ ታውቋል።
ጨዋታውንም ደቡብ አፍሪካዊው አቦንጊል ቶም በመሐል አልቢትርነት ሲመሩት አንጎላዊው ጄሰን ዶ ሳንቶስ እና ደቡብ አፍሪካዊው ዛክሄሌ ሲወላ በረዳትነት እንዲሁም የሀገራቸው ሰው የሆኑት ዩጂን ምድሉሊ በአራተኛ ዳኝነት ግልጋሎት እንደሚሰጡ ታውቋል።