በቅርቡ ከመቻል ጋር ስምምነት አድርጎ የነበረው አቤል ያለው ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ ለማምራት ከጫፍ ደርሷል።
ከኢትዮጵያ ውጭ በግብፁ ሊግ በዜድ ክለብ የነበረውን ቆይታ በስምምነት ያጠናቀቀው አቤል ያለው በሀገር ቤት ለመጫወት በቅርቡ ከመቻል ጋር መስማማቱ ይታወቃል። ሆኖም ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባገኘችው መረጃ ወደ ፈረሰኞቹ ቤት ለመመለስ ጫፍ ላይ መድረሱን አረጋግጣለች።
አቤል በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት የሊጉን ዋንጫ በማንሳት ስኬታማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን በድጋሚ ወደ ክለቡ የሚመለስን ዝውውር እያከናወነ እንደሆነ እና ዝውውሩ ዛሬ አልያም በቀጣዮቹ ቀናት የሚጠናቀቅ መሆኑን አውቀናል።
የቀድሞ የሐረር ሲቲ፣ ደደቢት፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች የነበረው አቤል ወደ ግብፅ አምርቶ በዜድ ክለብ የእግርኳስ ህይወቱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ዳግም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ወደ ቀድሞ ቤቱ ፊርማውን ያኖራል።