ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ውሉን አራዘመ

ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ ውሉን አራዘመ

የአቤል ያለውን ዝውውር እየፈፀሙ የሚገኙት ፈረሰኞቹ የግራ መስመር ተከላካያቸውን ውል ማራዘማቸው ታውቋል።

በአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የነባር ተጫዋቾችን ውል እያደሱ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው እያመጡ እንደሆነ ይታወቃል። በመቀጠል ደግሞ የወጣቱን የግራ መስመር ተከላካይ ውል ማራዘም መቻላቸውን አውቀናል።

ከሀሌታ ፕሮጀክት የተገኘው ሻይዱ ከኮቪድ በኋላ የፈረሰኞቹን ታዳጊ ቡድን በመቀላቀል በሂደት ወደ ዋናው ቡድን መጫወት የቻለ ሲሆን በተለይ በተጠናቀቀው የውድደር ዓመት ለቡድኑ ባደረጋቸው 25 ጨዋታዎች 2145 ደቂቃዎች በማገልገል ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት እንደነበረ አይዘነጋም። አሁን ከአሳዳጊ ክለቡ ጋር ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት መስማማቱን ሰምተናል።