ታሪካዊው ተጫዋች ረዳት አሰልጣኝ ሆኗል

ታሪካዊው ተጫዋች ረዳት አሰልጣኝ ሆኗል

የቀድሞው የዋልያዎቹ ኮከብ እንዲሁም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለታሪክ ተጫዋች ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ ሰኞ ዕለት ከተሰባሰቡ በኋላ በትናንትናው ዕለት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች አሁን ደግሞ የቀድሞ ባለ ታሪክ ተጫዋቻቸውን በረዳት አሰልጣኝነት ሾመዋል።

በተለይም በሀዋሳ ከተማ ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ በወልቂጤ ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በመሰለፍ እና በመጫወት እንዲሁም ከፈረሰኞቹ ጋር በተደጋጋሚ የሊጉን ዋንጫዎች በማንሳት በሀገራችን ከሚጠቀሱ ባለ ታሪክ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው አዳነ ግርማ በቀድሞ ቡድኑ ውስጥ በቡድን መሪነት ሲያገለግል ከቆየ በኋላ አሁን ደግሞ በረዳት አሰልጣኝነት መሾሙን ሰምተናል።

* አዳነ ግርማ በቅርቡ የካፍ “ቢ” ላይሰንስ ስልጠና ወስዶ ማጠናቀቁ ይታወሳል።