ሴናፍ ዋቁማ ወደ አሜሪካ ታመራለች

ሴናፍ ዋቁማ ወደ አሜሪካ ታመራለች

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አጥቂ አመሻሹን ወደ አሜሪካ ታመራለች።

ሐምሌ 30 ከአሜሪካው ክለብ ዲሲ ዩናይትድ የሙከራ ዕድል ያገኘችው የመቻሏ አጥቂ ሴናፍ ዋቁማ የተሰጣትን ሙከራ  ለመጠቀም ወደ አሜሪካ ታመራለች።

ከዚህ ቀደም በጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት አካዳሚ፣ አዳማ ከተማ ፣ መቻል፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የተለያዩ የዕድሜ እርከኖች የተጫወተችው እና በግሏ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆና ያጠናቀቀችውና የሊጉን ዋንጫ ያነሳችው አጥቂዋ የቀረበላትን የሙከራ ዕድል በመጠቀም ከቀድሞ አጣማሪዋ ሎዛ አበራ ጋር ዳግም ለመጫወት የሚስችላትን ዕድል ለማግኘት በዛሬው ዕለት ከብሔራዊ ቡድን ስብስብ ተለይታ አመሻሹን ወደ አሜሪካ ታመራለች።

ሴናፍ በአሜሪካ የሙከራ ጊዜዋን በአስር ቀናት ውስጥ አጠናቃ ዳግም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ብሔራዊ ቡድኑን ትቀላቀላለች ተብሎ ይጠበቃል።