የጦና ንቦቹ ሁለት ተጫዋች ከከፍተኛ ሊግ ለማስፈረም ተስማሙ

የጦና ንቦቹ ሁለት ተጫዋች ከከፍተኛ ሊግ ለማስፈረም ተስማሙ

በአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ የሚሰለጥኑት ወላይታ ድቻዎች ሁለት ተጫዋቾች ለማስፈረም መቃረባቸው ታውቋል።

በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ በመጀመርያው ዙር ማጣርያ በደርሶ መልስ ውጤት በሊቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ከውድድሩ ውጭ የሆኑት ወላይታ ድቻዎች ሙሉ ትኩረታቸውን ለሀገር ውስጥ ውድድር በማድረግ የሊጉን የመጀመርያ ጨዋታ ለማድረግ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። አስቀድሞ በዝውውሩ መስኮቱ ነባር እና አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረሙት ድቻዎች አሁን ደግሞ ፈራሚያቸውን ከከፍተኛ ሊግ ሁለት ተጫዋቾችን አድርገዋል።

ቡድኑ ለመቀላቀል የተስማማው የመጀመርያ ተጫዋች ኪዳኔ አሰፋ ነው የእግርኳስ ሕይወቱን በዲላ ከተማ የጀመረው ሁለገቡ ተጫዋች ከዚህ ቀደም በጅማ አባ ቡና ፣ ደቡብ ፖሊስ ፣ ሀላባ ፣ ስሑል ሽረ፣ ሰበታ ከተማ ፣ ሀምበርቾ በተጠናቀቀው ዓመት በንብ ጥሩ ጊዜ ያሳለፈ ሲሆን አሁን ማረፊያው ወላይታ ድቻ እንዲሆን ተስማምቷል።

ሌላኛው ተጫዋች አጥቂው የኋላሸት ሰለሞን ነው በፕሪሚየር ሊጉ በወልቂጤ ከተማ እና በሀዲያ ሆሳዕና ሲጫወት የምናውቀው አጥቂው ባሳለፍነው ዓመት በሀላባ ከተማ ቆይታ ያደረገ ሲሆን አስር ጎሎችንም በማስቆጠር ከፍተኛ ጎል አግቢነትን ሲፎካከር ነበር። በመጨረሻም በወልቂጤ ከተማ አብረውት የሰሩትን አሰልጣኝ ገብረክርስቶስን ዳግም በወላይታ ድቻ ለማግኘት መቃረቡን ሰምተናል።