በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሩዋንዳዊ አጥቂ ለማስፈረም ተስማምቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ተሳትፎ ያደረገው እና አስቀድሞ በዝውውር መስኮቱ በረከት ወልደዮሐንስ፣ ቤዛ መድኅን፣ ሀሰን ሑሴን ፣ ሀቢብ ጃለቶን እና የቶጎ ዜግነት ያለውን ግብ ጠባቂው ዮሱፍ ሞሮይ አስፈርሞ የስምንት ነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘመው ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሁን ደግሞ ሩዋንዳዊውን አጥቂ ፓትሪክ ሲቦማና ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
በሊግ ደረጃ የእግርኳስ ሕይወቱን በሀገሩ ክለብ ኢሶንጋ የጀመረው ይህ አጥቂ ለሀገሩ ክለቦች ኤ ፒ አር እና ሙኩራ ቪክቶሪ ፣ ለታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ለቤላሩሱ ሶሊጎርስክ ፣ ለሞዛምቢኩ ፌሮቪያሪዮ ዳ ቤይራ እንዲሁም ለሊቢያዎቹ አል ኢቲሃድ እና አል ዋህዳ የተጫወተ ሲሆን 1 ሜትር ከ80 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው አጥቂ አሁን መዳረሻውን የኢትዮጵያው ክለብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አድርጓል።