በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ የሚመራው ሲዳማ ቡና ዩጋንዳዊ ግብ ጠባቂ ማስፈረሙ ታውቋል።
ከከፍተኛ ሊግ እና ከሊጉ የተወሰኑ ተጫዋቾችን በማስፈረም እንዲሁም የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በማራዘም ቅድመ ዝግጅት ጊዜያቸውን በማገባደድ ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች ዩጋንዳዊውን የግብ ዘብ ማስፈረማቸው ታውቋል።
ግብ ጠባቂ ኢማኑኤል ካልዮዋ በሀገሩ ክለብ ኤክስፕረስ የእግርኳስ ሕይወቱን የጀመረ ሲሆን በመቀጠል በኬንያው ቼሜሊል ሹጋር የአንድ ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ለልዌዛ ፣ ቡል ፣ ቪላ ክለቦች ከተጫወተ በኋላ ወደ ታንዛኒያ አምርቶ ለኪዮቩ ስፖርትስ አንድ ዓመት ቆይታ አድርጎ ነበር። በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የእግርኳስ ሕይወቱን ወደ ጀመረበት ኤክስፕረስ ተመልሶ የተጫወተ ሲሆን አሁን ማረፊያው ሲዳማ ቡና ሆኗል።
