የአዲስ አበባ ከተማ የሕዳሴ ዋንጫ ባለድል የሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የተከላካይ አማካይ ለማስፈረም ተስማምተዋል።
በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ በዝውውር መስኮቱ አጥቂውን ቡአይ ኩዌት፣ አማካዩን አበባየሁ ዮሐንስ ፣ የመስመር ተከላካዩን መሳፍንት ጳውሎስ፣ የመሃል ተከላካዩን ጥዑመልሳን ኃይለሚካኤል እንዲሁም ላለፉት ዓመታት በግብፁ ‘Zed’ ቆይታ የነበረው አጥቂው አቤል ያለውን በማስፈረም እና የነባር ተጫዋቾች ውል ያራዘሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ባለድል መሆናቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የተከላካይ አማካዩ ብርሃኑ አሻሞን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል።
ከደደቢት ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ወደ ወልዋሎ አምርቶ ቡድኑን ወደ ፕሪሚየር ሊግ እንዲያድግ ጉልህ አስተዋጾ ካደረጉ ተጫዋቾች አንዱ የነበረው ተጫዋቹ ባለፉት ዓመታት በሲዳማ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ሀምበርቾ፣ ሻሸመኔ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን በ2017 የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ንብ ከነበረው ጥሩ ቆይታ በኋላ ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል ከስምምነት በመድረስ የሕክምና ምርመራውን እያደረገ ሲሆን ነገ በይፋ ፊርማውን የሚያኖር ይሆናል።