ፈረሰኞቹ ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ፈረሰኞቹ ተከላካይ ለማስፈረም ተቃርበዋል

ከሁለት ክለቦች ጋር በተከታታይ ሁለት የሊግ ዋንጫ ያነሳው ተከላካይ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለማምራት ተቃርቧል።

የሊጉን ውድድር ከመጀመራቸው አስቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዳሴ ዋንጫን በማንሳት የተነቃቁት ፈረሰኞቹ ቡድናቸውን ለማጠናከር ከደቂቃዎች በፊት የተከላካይ አማካይ ብርሃኑ አሻሞን ለማስፈረም መስማማታቸውን አስነብበናችሁ ነበር። በመቀጠል ደግሞ ተከላካይ አሚኑ ነስሩን ለማስፈረም መስማማታቸውን አውቀናል።

ከጅማ አባ ጅፋር እና መቐለ 70 እንደርታ ጋር ለተከታታይ ዓመት ሁለት ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ያሳካው እና በመቀጠል ወደ በመቻል አምርቶ ቆይታ ያደረገው ተከላካዩ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ በሀላባ ከተማ በግሉ ድንቅ የውድድር ጊዜን ያሳለፈ ሲሆን አሁን ፈረሰኞቹን ለአንድ ዓመት ለማገልገል ተስማምቷል።