ወልዋሎዎች ናይጄርያዊ አጥቂ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል

ወልዋሎዎች ናይጄርያዊ አጥቂ ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል

ግዙፉ ናይጀርያዊ አጥቂ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል ተቃርቧል

 

ባለፉት ሳምንታት የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የቆዩት በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ የሚመሩት ወልዋሎዎች ናይጄርያዊ አጥቂ ለማስፈረም ተቃርበዋል። ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማው ተጫዋች ደግሞ የ23 ዓመቱ ሳሙኤል አያንሪንዴ ነው፤ ከዚህ ቀደም በክዋራ ዩናይትድ፣ ስፖርቲንግ ሌጎስ፣ ሹቲንግ ስታርስ እና ኬንያ ፖሊስ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ በፊት አጥቂነት እንዲሁም በመስመር መሰለፍ የሚችል ሲሆን ሀገሩን ወክሎም በቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ መሳተፍ ችሏል። ተጫዋቹ ቢጫዎቹን ለመቀላቀል መስማማቱን ተከትሎ ዛሬ አመሻሽ አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በዕለተ ሰኞ የህክምና ምርመራውን አጠናቆ በይፋ ቡድኑን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል።