አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ስብስባቸውን አሳወቁ

አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ስብስባቸውን አሳወቁ

ለ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅደመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ጨዋታ ያለው ዋልያው ስብስቡ ይፋ ሆኗል።

ታኅሣሥ 27 2018 አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን የዋልያዎቹ አለቃ አድርጎ የሾመው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለየት ባለ መልኩ (በቀጥታ ስርጭት) ለሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጨዋታ የተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂዎች

አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)
ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ ከተማ)
ሰኢድ ሀብታሙ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች

ዓለምብርሀን ይግዛው (መቻል)
አሥራት ቱንጆ (ድሬዳዋ ከተማ)
ያሬድ ካሣዬ (ኢትዮጵያ መድን)
አብዱሰላም ዩሱፍ (ድሬዳዋ ከተማ)
ያሬድ ባዬ (ሲዳማ ቡና)
ራምኬል ጀምስ (ኢትዮጵያ ቡና)
ምኞት ደበበ (ፋሲል ከነማ)
ግሩም ሀጎስ (መቻል)

አማካዮች

ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ)
ጋቶች ፓኖም (አል አረቢ / ሳዉዲ አረቢያ)
ብሩክ እንዳለ (ወልዋሎ ዓ/ዩ)
ብዙዓየሁ ሰይፈ (አዳማ ከተማ)
ወገኔ ገዛኸኝ (ኢትዮጵያ መድን)
ቢንያም አይተን (አዳማ ከተማ)

አጥቂዎች

ቸርነት ጉግሳ (መቻል)
መስፍን ታፈሠ (ሲዳማ ቡና)
አቡበከር ሳኒ (አዳማ ከተማ)
ካቤ ብዙነህ (ነጌሌ አርሲ)
አቤል ያለው (ሲዳማ ቡና)
ከነዓን ማርክነህ (አልሻባብ / ኦማን)

ጥሪ የተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች የሊጉ ውድድር እሁድ ከተጠናቀቀ በኋላ በቀጣዮቹ ቀናት ዝግጅታቸውን በይፋ እንደሚጀምሩ ተመላክቷል።